የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2016 ዓም የሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሂዷል።

ማገልገል ክብር መሆኑን በመረዳት ፐብሊክ ሰርቫንቱ የተጣለበት ሀላፊነት በትጋት መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2016 ዓም የሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሂዷል።

በእለቱም የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንደገለፁት ፐብሊክ ሰርቫንቱ የተጣለበት ህዝባዊና መንግስታዊ አደራ በብቃትና በንቃት ለመወጣት ተቋማዊ አሰራሮችና አደረጃጀቶች የለውጥ መሳሪያ በማድረግ የህዝባችን ተጠቃሚነትና ርካታ ይበልጥ ማጠናከር ይጠበቅበታል ።

እንደ ወረዳው መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች መፍቻ ስልት በመቀየስ በየተለያየ ደረጃ እቅዶች አቅዶ በየመዋቅሩ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ በርካታ ስኬታማ መከናወናቸውና እየተከናወኑ እንደሚገኙም ም/አስተዳዳሪ ጨምረው ገልፀዋል።

በቀጣይም የዲሲፕሊንና የአገልጋይነት ስሜት መጓደል እንዳይስተዋል መስራት ይጠበቃል ያሉት አቶ ተጠምቀ ፐብሊክ ሰርቫንቱ የተጣለበት የህዝቡን አደራ በታማኝነት ፡ በቅንነት ፡ በመሰጠትና በአገልጋይነት ስሜት እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የእዣ ወረዳ ብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰለሞን ዘርጋ እንዳሉት የፐብሊክ ሰርቫንቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት በቀጣይነትና በዘላቂነት ለማሻሻል ማቀድ ፡ መተግበር ፡ መገምገምና መሸለም የሚለው የእቅድ ዑደት መትከል ይገባል።

የዚህ መድረክ ዋና አላማው ተቋማት እና በግለሰቦች መካከል ያለው የአፈፃፀምና ክህሎት ልዩት ማቀራረብ ፡ በላቀና በትጋት ያገለገለን አገልጋይ ለማመስገን እንደሆነም ሀላፊው አመላክተዋል ።

ፐብሊክ ሰርቫንቱ ሚሰጠው አገልግሎት ወቅቱን የዋጁ የቀለጠፉና የማህበረሰቡ ፍላጎት ማሟላት የቻሉ እንዲሆን ለማስቻል አገልግሎት አሰጣጣችን ነገን የወለዱ ሳይሆኑ ዛሬ እንዲያልቁ በማድረግ ቴኬኖሎጂ ተኮር አገልግሎት ልንሰጥ እንደሚገባም አቶ ሰለሞን አስገንዝበዋል።

በእለቱም እንደ ወረዳው ግንባር ቀደም ከሆኑት መካከል የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤትና የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽንጉዳዮች ፅ/ቤት የተቋምና የባለሙያ ምርጥ ተሞክሮ ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦአል ።

በ2016 በጀት ዓመት ግንባር ቀደም በየተቋሙ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ ባለሙያዎች ፡ በተመሳሳይ መልኩ ከአጠቃላይ ወረዳው ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ ባለሙያዎችና ሴት የመንግስት ሰራተኞች የገንዘብ እና የእውቅና ሰተፊኬት ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በተቋማት ደረጃ የእዣ ወረዳ ፋኢል ፅ/ቤት ፡ አስተዳደር ፅ/ቤት እና የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤቶች በቅደም ተከተላቸው መሰረት ከ1ኛ – 3ኛ ደጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸው ሲል የዘገው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።