መስከረም 10/2019 ዓም
ቦዠባር ገበያ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ቦዠባር ከተማ ላይ የምትገኝ አንጋፋና ግዙፍ ገበያ ናት ።
የቦዠባር ከተማ ስራስኪያጅ አቶ ሲሳይ ሽምሳ ስለ ቦዠባር ከተማና በውስጧ የምትገኘው ስመጥር የቦዠባር ገበያ ጥቂት እንዲሉን ጠይቀናቸው ነበር ።
ከተማው ከእዣ ወረዳ ዋና ከተማ አገና ከተማ በ 27 ኪሜ ርቀት እንደምትገኝና የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች አማካኝ በመሆኗ ብዙ እንግዶች እንደምታስተናግድም ነግረውናል ።
በቦዠባር ከተማ ጉያ ስር የምትገኘው ቦዠባር ገበያ ትልቅ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም ይካሄድባታልም ብለዋል።
ከተማውን ቀድሞ ከነበረችበት ይበልጥ እንድትለማ ከነዋሪዎቿ ጋር በመሆን እጅግ ጠንካራ ስራዎች መከናወናቸውን አጫውተውናል።
በዚህ ገበያ ከጥቃቅን ነገሮች እስከ ትላልቅ የገበያ ግብዓቶች ግብይት የሚፈፀምባት ሲሆን ከብቶች ፡ ገብስ ፡ ጎመን ፡ አተር ፡ ነጭ ሽንኩርት እና የመሳሰሉት መጥቀስ ይቻላል ።
በዚህ ገበያ በዙሪያዋ የሚገኙ አርሶአደሮች ያመረቱትን ለአብነት ከ15 እስከ 20 መኪኖች በሳምንት ከዚህ ገበያ ገብስ ጭነው ይወጣሉ ፡ በተመሳሳይ መልኩ ለአዲስ አበባም ጭምር ትልቁ የጎመን አቅርቦት ከዚህ ከተማ እንደሆነም አቶ ሲሳይ ነግረውናል።
በአጠቃላይ ስለከተማ የልማት እንቅስቃሴ ቀጣይ የምንመለስበት ሲሆን እኛም እጅግ የገረመን በዚህ ገበያ የቤት በርና መስኮት ሳይቀር አጠቃላይ በገበያ አለም ላይ የሚገኙ ከትንሽ እስከ ትልቅ ቁሳቁሶች በገበያው ማግኝት እንደሚቻልም አረጋግጠናል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ በማለት አቶ ሲሳይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።











