የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

“የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት”

“የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት” በሚል ሀሳብ ለ4ኛ ዙር ለሚሰጠው የአባላት ስልጠና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አስታወቀ።

የእዣ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተሾመ ስራኒ እንዳሉት ስልጠናው የፓርቲው አባል አቅም ከመገንባት ባሻገር አመራሩና መላው አባላቱ የጋራ አስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፍጠር ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን ትልቅ አቅም መገንቢያ ነው ።

እንደ ወረዳው 10 ሺህ 239 አመራርና አባላት እንደሚገኙ የጠቆሙት ሀላፊው ከሚቀጥለው ጥቅምት 27/2017 – ጥቅምት 29/2017 ዓም በቀበሌ ማዕከላት ፡ በከተሞች እንዲሁም በወረዳው ማዕከል ለሚገኙ ፐብሊክ ሰርቫንት አባላት እንደሚሰጥም ጨምረው ተናግረዋል።

ይህም ስልጠና ለመስጠት ለአሰልጣኞች ኦረንቴሽን አስቀድሞ መሰጠቱን የጠቆሙት አቶ ተሾመ ከዚህ በተጨማሪ በሁሉም ማዕከላት የመሰልጠኛ አዳራሾችና ለስልጠናው ሚያስፈልጉ ጉዳዮች ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ገልፀዋል።