የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የህፃናት ተሳትፎ በማጎልበት የህፃናት ፓርላማ ማጠናከር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ።

የህፃናት ተሳትፎ በማጎልበት የህፃናት ፓርላማ ማጠናከር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የህፃናት ፓርላማ የ2017 ዓ.ም ጉባኤ አደረገ ።

የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ በጉባኤው ተገኝተው እንደገለፁት ህፃናት መብቶቻቸውን ለማስከበር ፡ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅና ተግባራዊነቱን ለማሳካት እንደ እድሜያቸዉ ደረጃና የአስተሳሰባቸው ብስለት በመረጥዋቸዉ ጉዳዮች መወያየት ይችላሉ ብለዋል።

ለህፃናት ልዩ እንክብካቤ በማድረግ ህገ_መንግስታዊ መብታቸውን በማስጠበቅ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ በመፍጠር ትልቅ ትርጉም ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጨምው የገለፁት ሀላፊዋ ይህም የመላው ማህበረሰብ ትኩረት የሚሹ በመሆናቸው በዚህ በለጋ እድሜያቸው የሁላችንም ክትትልና ትኩረት ይፈልጋሉ ብለዋል ።

በቀጣይም በወረዳችን የሚገኘው የህፃናት ፓርላማ የህፃናት ድምፅ በመሆን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ጥሩ እንቅስቃሴዎች በማድረግ የሚታዩ ክፍተቶች በመለየት ከቀበሌ ጀምሮ እገዛና ክትትል በማጠናከር ጠንካራ ስራ እንደሚሰራም ወ/ሮ አሰለፈች ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ወረዳ የህፃናት ፓርላማ አፈጉባኤ ተማሪ አለውያ ሀሰን በወረዳው ህፃናት ፓርላማ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የህፃናት መብት ጥበቃ እና መብቶች ዙርያ የድጋፍና የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩም ቢሆንም በሚጠበቀው ደረጃ ከማጠናከር አንፃር ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም የህፃናት ፓርላማ ሲጓደል ቶሎ ከማስተካከል አንፃር ውስንነት ያሉትን ውስንነቶች በመጥቀስ ሊስተካከል እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የህፃናት ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ተማሪ ዮርዳኖስ ፍቅሬ በበኩላቸው ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢዎች ከመሆናቸው አንፃር እንደዚህ አይነት መድረኮች ላይ በመሣተፍ አሰራርና ስርዓት እንዲለማመዱ አቅማቸው እያሳደጉ እንዲሄዱ እንደሚጠቅማቸው ገልፀዋል።

በቀጣዮም በህጻናት ላይ የሚደርሱ በደሎችን የመለየት እና ጥቃቶችን ጥቆማ ለማድረግ የህፃናት ፓርላማ ከህብረተሰቡ ጋር በርካታ ስራዎች መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በኤለቱም የህፃናት መብት ጥበቃ እና መብቶች ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በአቶ ከበደ ቢረዳ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በጉባኤውም መጨረሻ የተጓደሉ ስራ አስፈፃሚና የጉባኤ አባላት የመተካት ስራ ተከናውኗል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።