







በሆስፒታሉ የእየተከናወኑ የሚገኙ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠልና የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
የካቲት 9/2018 ዓም
የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቦርድ አመራር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ስራ አፈፃፀም ገምግሟል።
የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊና የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ አመተረኡፍ ሁሴን እንዳሉት መንግስት ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ከሚያከናዉናቸው ተግባራቶች አንዱ የህክምና ተቋማት መገንባት አንዱ ሲሆን የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲገኙ በማድረግ የተለያዩ እንግልቶች እንዲቀረፍላቸው አስችሏል ።
በሆስፒታሉ በባለፈው የቦርድ ውይይት የተነሱና የተቀመጡ ዋና ዋና ሀሳቦች እንዲሁም ማነቆዎች ለመፍታት ጥረት መደረጉንም በጥንካሬ የሚታይ መሆኑንም የቦርድ ሰብሳቢዋ ገልፀዋል ።
የውስጥ ባለሙያዎች ከማወያየት ጀምሮ የሰው ሃይል እጥረት ለመፍታት ባለሙያዎች መቀጠራቸውን ፡ ከግብአት አቅርቦት ፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳዮች አንፃር እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታቱ ናቸው ያሉት ወ/ሮ አመተረኡፍ በቀጣይም በሆስፒታሉ ያሉ ጉለቶች እንዲቀረፉ በማድረግና ማህበረሰቡ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ጠንካራ ስራ መስራት ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማጠናከርና ተጨማሪ ሚያስፈልጉ ጉዳዮች እንዲሟሉ ወረዳውና አጋር ድረጅቶች እንዲሁም ማህበረሰቡን በማሳተፍ የአገልግሎት ደረጃው ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በቀጣይም በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የተለዩት ጉለቶች እንዲፈቱ እና መልካም አፈፃፀሞች በማጠናከር በትኩረት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በሆስፒታሉ በዋና ዋና ተግባራቶች እና ከሪፎርም ስራዎች አንፃር እንዲሁም በተቋሙ አቅም መፈታት የሚችሉ ጉዳዮች ከመፍታት አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም አሁን ጥረት የሚጠይቁ በመሆናቸው በተቀናጀ መንገድ መስራት እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ የእናቶች ኮንፈረንስ መደረጉ እጅግ የሚበረታታና እናቶች ወደ ተቋሙ መጥተው እንዲያርፉ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ለሌሎችም ጤና ተቋማት ተሞክሮ የሚሆን ነው ያሉት አቶ ዘውዱ በቀጣይም የገጠሙ ጉዳዮች መሰረታዊ ምክንያታቸው እንዲታወቁ በማድረግ ፡ አንዳንድ መሟላት ያሉ ጉዳዮችና ግብዓቶች ከዞን ጀምሮ መፈታት ያለባቸው ሀላፊነት በመውሰድ ፡ የጎደሉ የህክምና ግብዓቶች በተለያዩ አካላት እየተሟላበት ያለው መንገድ በማጠናከር ሆስፒታሉ የሚጠበቅበት አገልግሎት እንዲሰጥ በትኩረት መስራት ይገባልሞ ብለዋል ።
የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ሸምሱ ከድር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በሆስፒታሉ የአገልገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ርብርብ መደረጉን ተከትሎ እየተሰጠው ያለው የህክምና አገልግሎት እየተሻሻለ መምጤቱን ጠቁመዋል ።
በቀጣይም የበሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማሻሻል ፡ የማኅበረሰብ ባለቤትነትና መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል ፡ የህክምና አገልግሎቶች አሰጣጥ ማሻሻል እና ሌሎችም ተግባራቶች በላቀ ደረጃ ለመፈፀም ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ሸምሱ በሂደቱም ያልተሟሉ የህክምና ግብዓቶች እንደ ወትሮው መንግስት ፡ ረጂ ድርጅቶችና ማህበረሰቡ በማሳተፍ ሆስፒታሉ በተሟላ የህክም እንዲሁም ግብዓትና በተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።
ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በሆስፒታሉ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ያከናወናቸውን አበረታች ተግባራቶች በላቀ ደረጃ በማስቀጠል እና በአፈፃፀም ወቅት የተለዩትን ጉለቶችን በማረም ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።







