










የእዣ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ለሀገር ሰላም ለማስከበር ግንባር ለሄደው የዘማች ቤተሰቦች ድጋፋን አጠናክረው እንደሚቀጥል ገለፀ።
የወረዳው ሚሊሻ ፅ/ቤት ከወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት አባላት ጋር በመተባበር በወረዳ ሸብራደን ቀበሌ ለዘማች ቤተሰብ የእርሻ ስራና የግንዘብ ድጋፍ አድርጓል ።
የእዣ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አንዳርጋቸው ኪዳኔ ድጋፍ በተደረገበት ወቅት እንደገለፁት ዘማቾች ሀገርን ከወራሪ ሀይል ለመታደግ በግንባር ሲዋደቁ እኛ አቅማችን በፈቀደው መልኩ ደጀን በመሆን የዘማች ቤተሰብ በመርዳት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ልንቆም ይገባል ብለዋል።
በዛሬው እለትም በወረዳው ሸብራደን ቀበሌ ግቢ ሻም የሚገኙት ወ/ሮ ደመቀች ሽኩር ልጃቸው ከ2ዓመት ጀምሮ የሀገር መከላከያ በመቀላቀል የሀገር ዳርድንበር ለመጠበቅ መቀላቀሉን ተከትሎ የወረዳው ሚሊሻና ፖሊስ አባላት ከጎናቸው እንደሆነ ለማሳየት መሆኑንም ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል።
እንደ ወረዳ ይህ ድጋፍ በተለያየ ጊዜ እየተደረገ እንደሆነ የገለፁት አቶ አንዳርጋቸው የሚሊሻና ፖሊስ አባላት ድጋፋቸውን በሌሎችም አካባቢዎች አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል ።
እርሻ በማረስ ድጋፍ ያደረጉት የወረዳው ሚሊሻና ፖሊስ አባላት በበኩላቸው እንዳሉት ለዘማች ቤተሰብ ድጋፍ የማድረግ ምክንያታችን ወገን የሀገርን ድንበር ለመጠበቅ ሲሄዱ እኛ ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍ በማድረግ ግንባር ላሉ ወገኖቻችን አጋርነታችንን ለመግለፅ ነው ብለዋል ።
ድጋፍ የተደረገላቸው የዘማች እናት ወ/ሮ ደመቀች ሽኩር ልጄ እኛ የምንኖረው ሀገር ስትኖር ነው ብሎ የሀገር መከላከያን ተቀላቅሎ ሀገሩን እየጠበቀ መሆኑንና በዚህም እጅግ ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀዋል።
የተደረገላቸው የእርሻና የገንዘብ ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።








