===============የእዣ ወረዳ አስተዳደር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል ።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በከብቶች በረት መወለዱን የምናስብበት እና በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ከመሆኑም ባሻገር ፍቅር ፡ አንድነትና እርስ በእርስ መረዳዳትን ጎልቶ የሚታይበት ታላቅ በዓል ነው።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ይህ በዓል በሰላምና በምድር ለሚገኙ ነገዶች የእልልታና የምስጋና ምንጭ የሆነው ነቢያት የተመኙት ፡ መላዕክት ያወደሱት ፡ እረኞች ያወሩለት ሰባ ሰገል የሰገዱለት ፡ ሀጥያተኞች የዳኑበት ግዞተኞች የተፈተኑበት ሀዋሪያት ያከበሩ ለሰዎችና ለመላዕክት ታላቅ ደስታ የሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን አስመልክተን የምናከብረው ታላቅ በዓል ነው፡፡
በልደቱ መደሰታችን ምክንያት ያለው ሲሆን ለሰው ልጆች ክፋትን ሳይሆን መልካምነትን ፡ የፃድቃን ስራዎችን ባህላችን እንዲሆኑ የምንጥርበት ነው ።
ስለሆነም በዓሉን ስናከብር በችግር ውስጥ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመደጋገፍ ፡ ያለው ለሌለው በማካፈል ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነታችንን የበለጠ እያጠናከርን ማሳለፍ እንዳለብንም ዋና አስተዳዳሪው መልዕክታቸው አስተላልፈዋል ።
በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆን እንመኛልን !!
መልካም በዓል!!








