





የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በማስመልከት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የዋኸንየ ት/ቤት መምህራንና ተማሪዎች በዓሉን በልዩልዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ አክብረውታል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት የሚካሄደው የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በማስመልከት ተቋማቶች በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩት ይገኛል።
በእዣ ወረዳም ይህንኑ በማስመልከት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተከበረ ሲሆን በዛሬው እለት ማጠቃለያ መርሃ ግብር ተከናውኗል ።
በእለቱም ህብረብሔራዊነትን የሚያጎሉ የስነፅሁፍ ስራዎች በተማሪዎች ለታዳሚያን የቀረበ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ስፖርታዊና የተለያዩ አዝናኝ ትዕይንቶች ቀርበዋል።







