





በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ የቆየው 4ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና ተጠናቋል።
ጥቅምት28/2017 ዓም
የእዣ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተሾመ ስራኒ እንደገለፁት ስልጠናው በፓርቲው እሳቤ አመራሩና አባሉ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ተረድቶ በተለያየ መንገድ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲያመጡ እንዲሁም በተግባር ላይ እንዲያውሉ የተሻለ ግንዛቤ የፈጠረ ነው ብለዋል።
ስልጠናው የአባሉን የአስተሳሰብ ፡ የአመለካከትና የስራ ተነሳሽነት እንዲሁም የስራ ክህሎት በማሻሻል ሀገራዊውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑ ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል ።
ጠንካራና ብቁ አመራርና አባል ለማፍራት ፓርቲው ከያዛቸው ዕቅዶች አንዱና ዋነኛው የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሆን ይህም ስልጠና ለአባሉ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠሩንም አቶ ተሾመ አመላክተዋል።
በየማህበራዊ ዘርፎች የተነሱትን ጥያቄና አስተያየቶች ሀላፊው ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በገዢ ትርክቶች ላይ መሰረት አድረገን የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እኖዲቀጥሉ አባሉ የራሱን ድርሻ መጫወት አለበትም ብለዋል።
ሰልጣኞችም በሰጡት አስተያየትም ፓርቲው የጀመራቸው የልማት ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆነ ተናግረው በቀጣይም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ልማቶች እንዲስፋፉ መንግስትና ህብረተሰቡ በመቀናጀት መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል።
በነገው እለትም 5ኛው አመት የብልፅግና ፓርቲ ምስረት ጉባኤ መላው አባሉ በተሟላበት እንደሚካሄድም ተጠቁሟል ።






