






በጉራጌ ዞን በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወሩ የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
ጥር 28/2018(ወልቂጤ)
በጉራጌ ዞን በፓርቲና በመንግስት የሚወርዱ ኢኒሼቲቮች ተቀብሎ ወደ ተግባር በመቀየር እረገድም በሁሉም ዘርፎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል።
በዞኑ በ6 ወሩ በመንግስትና በፓርቲ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው ሲሆን ሌሎች አካባቢዎች ልምድ የተወሰደባቸው መሆናቸው ተመላክቷል።
የአመራር የሀሳብና የአመለካከት አንድነት፣ቁርጠኝነትና አርቆ የማሰብ እሳቤ በማጽናት በተግባርም የተሻለ አፈጻጸም እንዲታይ አስችሏል ነው የተባለው።
በተያያዘም የህዝብና የመንግስት አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም ፣የዞኑ አቅምና ጸጋ ለይቶ በመስራት የማህበረሰቡ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ተብሏል።
ለአብነትም በጉራጊና ቋንቋ፣ በመንገድ፣በትምህርት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በጤና ፣በግብርና ፣በባህልና ቱሪዝም፣በሰላምና ጸጥታ እና በሌሎችም የተሰሩ ስራዎች ተጠቅሰዋል።
በ6 ወሩ የነበሩ ጠንካራ ስራዎች በማጠናከር የታዩ ችግሮች ደግሞ በማረም በቀጣይ ግማሽ አመት የበለጠ ስራ ለመስራት አላማ ያደረገ መድረክ ነው።
በመድረኩም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል ፣የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።






