የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የፖሊዮ በሽታ የመከላከያ ክትባት ዘመቻ በወረዳ አጓይተረህ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።

=====በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የፖሊዮ በሽታ የመከላከያ ክትባት ዘመቻ በወረዳ አጓይተረህ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።

የካቲት 14/2017ዓ.ም

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተገኙት የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ ፡ እንደገለፁት ለአራት ቀናት የሚቆየው የክትባት ዘመቻ በሁሉም የወረዳው ቀበሌዎች እድሚያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ 16 ሺህ 817 በላይ ህጻናት ክትባቱ የሚሰጥም ይሆናል ።

ሀላፊው አክለውም የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣና በዋናነት የህፃናትን ጤና በመጉዳት እስከሞት የሚያደርስ ሲሆን ክትባቱን በተገቢው መንገድ በመውሰድ በሽታውን መከላከል ያስችላል ።

ይህ ክትባቱ በዘመቻ መልክ ቤት ለቤት የሚከናወን ሲሆን ሕፃናቱ ከአሁን በፊት ክትባቱን ቢከተቡም ባይከተቡም አሁን የሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት መውሰድ እንደሚኖርባቸው አቶ መሀመድ ጨምረው ገልፀዋል ።

በዘመቻ መርሃ ግብሩም የወረዳ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ኮማንድ ፖስት በዳርቻ ጤና ጣቢያ በመገኘት የዘመቻው የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቶ ተግባሩ በታቀደው መልኩ እንዲሳካ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

በዘመቻ መርሀ ግብሩም የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ ፡ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ባለሙያ ወ/ሪት ዘይነባ ጀማል ፡ የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አመነ ፍቅሬ እንዲሁም የፅ/ቤቱ የዘመቻው አስተባባሪ ባለሙያዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሾን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።