





በፍጥነት የማድግ እድል ያለው ዳርቻ ዝግባቦቦቶ ማዘጋጃ ቤት
ዳርቻ ዝግባቦቶ በ2017 ዓ.ም የማዘጋጃ ቤት እውቅና ካገኘ ወዲህ በከተማው ማህበረሰቡና መንግስት በቅንጅት የተሰሩ የልማት ስራዎች አበረታች ናቸው።
ህዳር 2/2019 ዓም
የማዘጋጃ ቤቱ ስራስኪያጅ አቶ ታፈሰ ሳርሄ በከተማው የተጀማመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር ከተማዋ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ጠንካራ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል ።
በቅርቡም 6 ሚልዮን 517 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የዳርቻ ዝግባቦቶ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የአገልግሎት አሰጣጥ ምቹና ማራኪ ለማድረግ እንደሚያግዝም ስራስኪያጁ አመላክተዋል።
ታዳጊ ከተማዋ በሚፈለገው ልክ እንድታድግ በፕላን መሰረት መምራት እንደሚገባ በማመን መንግስት፣ ነዋሪውና ባለሀብቱ በማስተባበር ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን መሰራታቸውንም አቶ ታፈሰ አመላክተዋል።
ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ፣ ሳቢና ተስማሚ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ነዋሪዎችን በማሳተፍ ከ8ኪ.ሜ በላይ የጠጠር መንገድ ግንባታና ከ5መቶ ሜትር በላይ የመንገድ አካፋዮች ማልማት መቻሉንእ ገልፀዋል ።
በከተማው የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የሞዴል መንደር ምስረታ ግንባታ በፍጥነት እየተሰራ ሲሆን በንፁህ መጠጥ ውሃና ሀይል አቅርቦት ላይ ከወረዳው መንግስት ጋ በመቀናጀት ሰፊ ርብርብ እየተጀረገም ይገኛል ብለዋል።
በከተማው ዙሪያ ውጤታማና ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና ሚጫወቱ ኢንቨስትመንቶች መኖራቸው ከተማው በፍጥነት ለማደግ ምቹ አጋጣሚዎች ከሆኑት ጉዳዮች ይጠቀሳሉ ብለዋል ።
በአጠቃላይ በከተማ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎች ተስፋ ሰጪ ከመሆናቸዎ በተጨማሪ ከተማው ለማደግ ምቹ ሁኔታዎች ያሉ በመሆኑ ባለሀብቱ ወደ ከተማዎ በመምጣት በተለያዩ አማራጮች ኢንቨስት እንዲያደርግ አቶ ታፈሰ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።






