የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ትምህርት ቤቶች ሁለተናዊ እድገት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ ።

=======================================

ትምህርት ቤቶች ሁለተናዊ እድገት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ ።
በአገና ከተማ አስተዳደር የየስራይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቀድሞ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር የእድሳት ስራ ተጀምሯል።
የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ የእድሳት ስራው በተጀመረበት ወቅት እንደገለፁት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የትምህርት ማህበረሰቡ በየአካባቢው የሚገኙ ትምርት ቤቶች ግንባርቀደም ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል ።
የትምህርት ቤቶች ሁለተናዊ እድገት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነ የገለፁት ከንቲባው የየስራይ ትምህርት የቀድሞ የተማሪዎች ህብረት በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቱ ለማሳደስና ለማሳደግ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ብለዋል ።
ምቹ የማማሪያ ክፍሎች ፡ ፅዱና ሳቢ የሆነ የትምህርት ቤት አካባቢ መፍጠር የመማር ማስተማር ስርዓት ለማሻሻል ከሚረዱ ጉዳዮች አንዱ ነው ያሉት አቶ ሀብቴ የከተማው አስተዳደርም በሙያዊና በሌሎችም ጉዳዮች በማገዝ የድርሻውን ይወጣል ብለዋል።
ትምህርት ቤቱ እንዲያድግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ይህንን አላማ እንዲሳካ ርብርብ እያደረጉት ያሉ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ከንቲባው ስራው በተባለለት ጊዜ እንዲሳካ ማንም በሚችለው አቅም ለነገ ትውልድ ሲል ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የቀድሞው የየስራይ ትምህርት ቤት ህብት ሰብሳቢ አቶ አየለ ተሰማ በበኩላቸው እንደገለፁት ትምህርት ቤቱ ረጅም ዘመናት ከማገልገሉ የተነሳ እርጅና ተጫጭኖት የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ይህንን ችግር ያስጨነቃቸው በት/ቤቱ የቀድሞ ተማሪውች ጥረት የተጀመረው የእድሳትና የማሻሻል ሀሳብ በመንግሥት እና በህብረተሰቡ ተቀባይነት አግኝቶ ልበ ቀና በሆኑ የቀድሞ ተማሪዎች የገንዘብ መዋጮና በአገና ከተማ አስተዳደር እገዛ የመጀመሪያው ዙር የእድሳት ስራ መጀመሩንም አቶ አየለ አብራርተዋል ።
የትምህርት ቤቱ እድሳትና ማሻሻያ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ነው ያሉት አቶ አየለ በቀጣይም ትምህርት ቤት ካለበት ችግር ለማላቀቅና ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት እንዲሆን ሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተሾመ ፈቀደ የየስራይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1961 ዓ.ም የተመሠረተው ሲሆን በርካታ ለአካባቢው ብሎም ለሀገር እያገለገሉ የሚገኙ ምህራን ትውልድ ያፈራና በወረዳው ከሚገኙ አንጋፋ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚጠቀስ እንደሆነም አስረድተዋል።
ትምህርት ቤቱ ከብዙ ታሪካዊ የስኬት ጉዞ በኋላ በቅርብ አመታት ለብዙ ችግሮች ተጋልጦ የበረ ስለሆነ አሁን በቀድሞ ተማሪዎች እየተደረገውን ያለ እንቅስቃሴ ከነበረበት ማነቆ የሚያወጣው በመሆኑ ስራው እንዲሳካ ትኩረት ሰጥቶት ይሰራልም ብለዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ ትምህርት ፡ የእንስሳት ርባታ ስራ ፡ የፍራፍሬ ችግኞች የመትከልና ሌሎችም በተለያየ መልኩ ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተሾመ በቀጣይም ትምህርት ቤቱ በብዙ መልኩ ተለውጦ ውጤታማ እንዲሆን የመስራቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።