






የእዣ ወረዳ ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ የም/ቤት አባላት ለአረጋውያን ድጋፍ አደረጉ ።
የእዣ ወረዳ ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሰናይት ሳህሌ ድጋፍ በተደረገበት ወቅት እንደገለፁት ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር የተጋለጡትን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ ሁሉም ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት በመስጠት የእርስ በርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልና ልምዱን በማጠናከር በተደራጀ መልኩ መንቀሳቀስ ይገባል ፡፡
አፈ -ጉባኤዋ አያይዘውም ድጋፉም በ1ኛ ሩብ አመት ጉባኤ ወቅት በኮከሱ ከተቆጠበው ብርና በግል በማዋጣት እንዲሁም አልባሳት ከየቤቶቻቸው በመሰብሰብ በዛሬው እለት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
እንደ ወረዳው በተለያየ ችግር ምክንያት ድጋፍ የሚሹና አረጋውያን ለከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳይዳረጉ አቅም በፈቀደው ደረጃ ለማቋቋምና ለመርዳት በቀጣይም ምክር ቤቱ ድጋፉ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ወ/ሮ ሰናይት ገልፀዋል።
በዛሬው እለት ድጋፍ የተደረገላቸው አካላትም በቀራተሞ ቀበሌ ለከፋ ችግር የተጋለጡ አረጋውያኖች ፡ ማየት የተሳናቸውና የጤና ችግር ያለባቸው ወገኖቻችን የምግብ ፡ የአልባሳት እና የሻይ ቡና ዝግጅት በማድረግ በደምሩ 10,000ብር ድጋፍ የሴት የኮከስ አባላቱ ድጋፍ ማድረጉንም ገልፀዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸውም አካላት ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ብዙ ወገኖች በየአካቢው ስላሉ ቀጣይነት ባለው መልኩ ድጋፉ መጠናከር አለበት ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።







