የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት የ2016 ዓም የተሰሩ ስራዎች እና የ2017 ዓም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የመንገድ ልማት ስራዎችን በማጠናከር በ2017 ዓም በላቀ ደረጃ በማስቀጠል ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገለፀ ።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት የ2016 ዓም የተሰሩ ስራዎች እና የ2017 ዓም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በእለቱም እንደገለፁት መንገድ የልማት ሁሉ መሰረት መሆኑን በመገንዘብ እንደ ወረዳው በመንገድ ዘርፍ የወረዳው መንግስትና ህብረተሰብ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራ ተሰርቷል ።

በተከናወነው ጠንካራ ስራም አርሶአደሩ ያመረተው ምርት ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ልውውጥ በማድረግና ኑሮውን ለማሻሻል እድል ፈጥሯል ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው በተሰሩም ስራዎች ዘርፈ ብዙ ለውጦች መመዝገባቸውና ይህ ተግባር በዘንድሮ ዓመት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የወረዳው መንግስ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

ሌላው በትራንስፖርት ዘርፍ ህዝቡ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ለአንድ ሴክተር የሚፈታ ስላልሆነ የማህበረሰቡ ፡ የቀበሌ አመራር ፡ የትራፊክ ፖሊስ ፡ የባለሙያ ቅንጅትና ቁርጠኝነት በማቀናጀት ችግሩ እንዲቀንስ በባለቤትነት መሳተፍ ይገባልም ብለዋል ።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ መልስ በበኩላቸው እንደ ወረዳው ህብረተሰቡ በሰፊው የተሳተፈባቸው የወረዳው መንግስት ድጋፍ ያደረገባቸው የመንገድ ልማት ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ48 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ 40.7 ኪሜ የጠጠር መንገድ በተለያዩ ቀበሌዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በ2017 በጀት ዓመት መንግስት የህብረተሰቡ ችግር ለመፍታት እስከ 7.5 ሚሊየን ብር የመበጀት ስራ መሰራቱን የጠቆሙት ሀላፊው ይህም በቀጣይም የተበጀተው በጀት በታለመለት አላማ መሰረት እንዲከናወን የማህበረሰቡ ፡ የባለሀብትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተቋሙ የሚነሳው የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ኝግር ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራር በማቀናጀት ህብረተሰቡ አጋዥ ሆኖ ያላሰለሰ ጥረት መደረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ገዛኸኝ በዚህም በትምህርት ቤቶች ፡ በሀይማኖት ተቋማትና በገበያ ስፍራዎች የግንዛቤ ስራዎች በመስራት አስከፊው የሆነው የትራፊክ አደጋ ለመከላከልና የመልካም አስተደር ችግር ለመፍታት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

በእለቱም በተቋሙ የ2016 ዓም በዋና ዋና ተግባራት የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም የ2017 ዓም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰነዶች የፅ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጀንበር አክመል እንዲሁም አቶ አልዩ መሀመድ በኩል ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመጨረሻም በ2017 ዓም የላቀ አስተዋፅኦ ያደረጉት ባለድርሻ አካላት የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል ሲል የዘገበዎ የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።