የአመራርና የፈፃሚውን ቁርጠኝነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ የህዝቡ የጤና ባለቤትነት ተሳትፎው ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።
መስከረም 21/2016 ዓም
የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት አመታዊ ጉባኤ እና የ2017 በጀት ዓመት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።
በእለቱም መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አየለ ፈቀደ እንዳሉት የአመራርና የፈፃሚውን ቁርጠኝነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ የህዝቡ የጤና ባለቤትነት ተሳትፎው ማጠናከር ይገባል።
እንደ ዞኑ በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ስራዎች ማህበረሰቡ በተጨባጭ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል ያሉት ሀላፊው በዘርፉ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠልና ጉለት ያለባቸው ተግባራቶችንም ቶሎ እንዲታረሙ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
እዣ ወረዳ በጤናው ዘርፍ ለበርካታ አመታት በአፈፃፀም ግንባር ቀድም ሆኖ ለሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ጭምር ሞዴል ሆኑ ተሞክሮ የተቀመረበት ወረዳ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ አየለ ይህንን ተግባር ይበልጥ በማጠናከር ጥቂት በአፈፃፀም ወቅት የተለዩትን ጉለቶችን በማረም ጤናማና አምራች ማህበረሰብ እንዲጎለብት ጥረቱ ማጠናከር ይገባባዋልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው እንደ ወረዳው በጤናው ዘርፍ ህብረተሰቡ ራሱ የጤና ባለቤት ሆኖ ጤናማና አምራች ማህበረሰብ እንዲፈጠር በተከናወኑ ተግባራቶች አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
እንደ ወረዳው ማህበረሰቡ በማሳተፍ የመፀዳጃ ቤቶቻችን ደረጃ በማሻሻል እና ፅዱ አካባቢን በመፍጠር ለህክምናው የሚወጣው ወጪ መቀነስ ላይ ትኩረት ተሰጥቶታል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በአካባቢ ቁጥጥር ስራ የማህበረሰቡ ተሳትፎና የአጎበር አጠቃቀም በማሳደግ የወባ በሽታ ጫናን በመቀነስ እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ሞት ለመቀነስ የተከናወነው ስራ የሚበረታታ መሆኑንም አመላክተዋል።
ያለ ዜጎች ጤና ሌሎች የልማት ፡ የምርትና ምርታማነትና የብልፅግና ጉዳዮች ማሳካት የማይቻል በመሆኑ በንቃት መምራትና መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዘውዱ እንደ ወረዳው በ2016 በጀት ዓመት በአፈፃፀም ወቅት የገጠሙትን ጉለቶች በ2017 በጀት ዓመት ፈጥኖ በማረም በዘፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ እንዳሉት በወረዳው የተገኙ ውጤቶች ለማዳበር እና ለማስቀጠል ለወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት መፍጠር ስንችል ብቻ በመሆኑ ይህንንም ለማሳካት የሁሉም ድጋፍና ትብብር ይጠበቃል ብለዋል ።
በባለፈው በጀት አመት ከተከናወኑ ውጤታማ ተግባራቶች መካከል ሁሉም አይነት የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ከእቅድ በላይ መፈፀሙን ፡ ሁሉንም አይነት ያጠናቀቁ ህፃናቶ 98%መፈፀም ተችሏል ያሉት አቶ መሀመድ ከዚህ በተጨማሪ የእናቶችና ህፃናት ጤና ከማሻሻል አንፃር 208 እናቶች በእርጉዝ እናቶች ማረፊያ ቤት ተቀምጠው አገልግሎት በማግኘት 200 እናቶች በዚሁ ተቋም በሰላም ወልደው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሲሆን 8 እናቶች ሪፈር ያስፈልጋቸው ስለነበር የሪፈሪያል አገልግሎት ማግኘታቸውንና ሌሎችም በርካታ ጠንካራ ተግባራቶች መፈፀማቸውንም አብራርተዋል ።
በቀጣይም በትኩረት መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ለመቀነስ የወረደው የኢንሼቲቭ ማሳካት ፡ ከ12ሳምንት በፊት የቅድመ ወሊድ የሚጀምሩ እናቶች ማሳደግ ፡ በሳምባ ምች የታከሙ ህፃናት እና በተቅማጥ የታከሙ ህፃናት ዝቅተኛ መሆኑን ፡እድሜያቸው ከ0-59 ወር የስርዓተ ምግብ ልየታ የተደረገላቸው በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑ ፡ ሁሉንም አይነት የቲቪ ልየታ ዝቅተኛ መሆን ርብርብ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ በቀጣይ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ሀላፊው አሳስበዋል።
ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም እዣ ወረዳ ለብዙ አመታት በጤናው ዘርፍ ህብረተሰቡ ለማስጠቀም ሞዴል ወረዳ እንደሆነና ይህም ደረጃው ለማስጠበቅ በቁጭት መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
እንደ ወረዳው አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያጋጠመው የህክምና ቁሳቁስ እጥረት መላው ማህበረሰቡ በማሳተፉ ትኩረት ተሰጥቶት መስራት እንደሚያስፈልገውም አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው ተናግረዋል።
በጉባኤውም የ2016 ዓም የጤና አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የ2017 የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ በመወያየትና የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር በማካሄድ ጉባኤው ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው












