የኦሞ ባንክ አገና ቅርንጫፍ መጪው የሚከበረው የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
መስከረም 11/2019 ዓም
ተቋሙ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ፡ የደንበኞችን ቁጥር በመጨመር እና ጥራት ያለው የቁጠባና ብድር አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተጠቁሟል።
የኦሞ ባንክ አገና ቅርንጫፍ ስራስኪያጅ አቶ አሰፋ በረዳ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት ተቋሙ የተቀመጡለትን ዋና ዋና የባንክ ግቦች ለማሳካት ውጤታማ ስራ መስራቱን ገልፀው በተለይም የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ፡ የደንበኞችን ቁጥር በመጨመር እና ጥራት ያለው የብድር አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ።
በ2027 በጀት ዓመት ደግሞ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ይበልጥ በማስፋፋት ፡ የደንበኞችን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና የቅርንጫፉ የገበያ ድርሻ ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ስራስኪያጁ ጨምረው ተናግረዋል።
ተቋሙ ለህብረተሰቡ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አርሶ አደሮች ፡ ለሴቶችና ለስራ አጥ ወጣቶች ተጠቃሚ ለማድረግ ባደረገው ሰፊ ተግባር ውጤታማ ስራ መስራት ችሏል ያሉት አቶ አሰፋ በቀጣይም እየሰጠ ያለው አገልግሎት ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የኦሞ ባንክ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ተወዳዳሪና በአገልግሎት አሰጣጡ የተሻለ ባንክ እንዲሆን እያደረገው ባለው ጥረት የአገና ቅርንጫፍም የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነም ገልፀዋል።
ቅርንጫፉ አሰራሩና አደረጃጀቱን በማዘመን ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎቶችን በላቀ ሁኔታ እያቀረበ እንደሚገኝና በቀጣይም የበለጠ በማጠናከር በተለይም በብድር ስርጭትና አሰባሰብ ፡ የተረጋጋ ቁጠባ በማስቆጠብ ፡ አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት እንዲሁም ደንበኛው ባለበት አካባቢ ሆነው ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገው ያለው ጥረት በላቀ ደረጃ ይሰራል ብለዋል፡፡
የቅርንጫፉ ሰራተኞች በበኩላቸው የተሰጣቸውን ግብ ለማሳካት የነበራቸውን ጠንካራ ተሳትፎ በማጉላት በአዲሱ አመት የተጣለባቸውን ሀላፊነት በላቀ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መጪው የሚከበረው የ2019 ዓም የመስቀል በዓል ለመላው ደንበኞቹና ኢትዮጵያውያን መልካም በዓል እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።
መልካም የመስቀል በዓል!


















