ህዳር 7/2017 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያና የእዣ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በእዣ ወረዳ እየተሰሩ ያሉ የግብርና ልማት ስራዎች ጎበኙ።
እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ስራዎች የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአርሶ አደሩ እና የወጣቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆኑ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በእለቱም በተለያዩ ቀበሌዎች በሰብል ፣በችግኝ ማፍላት ፣በሮዝመሪ ፣ በነጭ ሽንኩርት ፣ በድንች ፣በዶሮ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ነው የታዩት።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በ2016/17 የምርት ዘመን ያላግባብ የተተከሉ ባህር ዛፎች ማንሳትና ለዘመናት ያልታረሱ መሬቶች እንዲታረሱ በትኩረት ሲሰራበት ነበር ብለዋል።
በዚህም 5ሺ 9መቶ ሄክታር መሬት ለዘመናት ያልታረሱ መሬቶች መታረሳቸው እና ዞኑ እምቅ የግብርና አቅም እንዳለው በሀገር አቀፍም ማሳየት ተችሏል።
አቶ አበራ አክለውም በእንስሳት እርባታ ፣በፍራፍሬ ልማት ፣በቡና ፣በሰብል ልማት፣በዶሮ ፣በንብ ማነብ፣በጤፍ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ተሰማርተው አርሶ አደሩ እንዲሁም ሴቶችና ወጣቶች የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ መሆኑ አስታውቋል።
ለአብነትም በዘርፉ ከ20 ሺ በላይ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን 1ሺ 2መቶ ሄክታር መሬት በወጣቶች ለምቷል ነው ያሉት።
በእነዚህ ምርቶች ሻጩና ሸማቹ በቀጥታ በማገናኘት ምርቱ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ በመደረጉ የኑሮ ግሽበቱ እንዲረጋጋ አስችሏል ብለዋል።
በዚህም የእዣ ወረዳ ለግብርና ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተከናወኑ የግብር ስራዎች እጅግ አመርቂ መሆናቸው የገለጹት አቶ አበራ በዛሬው እለት በተለያዩ ቀበሌዎች በሰብል ፣በችግኝ ማፍላት ፣በሮዝመሪ ፣ በነጭ ሽንኩርት ፣ በድንች ፣በዶሮ እርባታ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መመልከት ተችሏል።
የእዣ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቻል ተሰማ እንደገለጹት በወረዳው የአርሶ አደሩ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እና ወጣቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት ይሰራል።
በእንስሳት እርባታ ፣በጤፍ ፣በፍራፍሬ ልማት ፣በቡና ፣በጥራጥሬ ሰብሎች፣በችግኝ ማፍላት ፣ በዶሮ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ አብራርተዋል።
በምርት ዘመኑ ከ6 ሺ 4መቶ 35 ሄክታር መሬት በላይ በተለያዩ ሰብሎች የተሸፈነ ሲሆን 8 መቶ 90 ሺ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል አቶ መቻል።
በዘንድሮ አመት በወረዳው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ከ9 መቶ ሄክታር መሬት በላይ ያልታረሱ መሬቶች እንዲሁም 1 ሺ 7 መቶ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም መታረሱ አመላክቷል ኃላፊው።
ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ከቅድመ ዝግጅት ስራ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የቴክኖሎጂና የግብአት አቅርቦት የማመቻቸት ፣አፈርን በኖራ የማከም ፣ጸረ ተባይ ኬሚካል የመርጨት ፣የባለሙያ ድጋፍ ክትትል የማድረግ፣የገበያ ትስስር የመፍጠር ስራ መሰራቱ አስታውሰዋል።
አቶ መቻል እንደተናገሩት በወረዳው በግልና በማህበር በግብርና ዘርፍ ከተደራጁት ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል የሚያስመዘግቡ እንዳሉ ጠቁመዋል።
ወጣት አዳነ ብሩ በወረዳዉ በዶሮ እረባታ ያገኘነው ሲሆን በኢንጂነሪንግ የተመረቀ ቢሆንም ዛሬ ላይ 5 መቶ ዶሮዎች እያረባ በቀን ከ4መቶ 50 እስከ 5መቶ እንቁላል ለገበያ አቅርቦ ውጤታማ መሆኑ ተናግሯል።
ልሎች በወረዳው ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው በየጊዜው በራሳቸው ጥረት እና በመንግስት ድጋፍ በሰሩዋቸው የግብርና ስራዎች በኑሮዋቸው ላይ ለውጥ በማምጣት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆናቸው ገልጸዋል።