






ጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት እና እርግብ የትምህርት አገልግሎት ለ20 ቀናት ላሰለጠኗቸው መምህራን በደሳለኝ ሎጅ እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሂዷል ።
በመርሃ ግብሩ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማሪያም ፤የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ፡ የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ ፡ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ ፡ የአገና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ከልል ክብሩ ፡ የጋበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኮሬ ባዌ ፡ጨምሮ የወረዳውና ከተማ የተለዩ ሴክተር የስራ ሀላፊዎች የጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት እና እርግብ የትምህርት አገልግሎት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።
ድርጅቱ በሀገራችን ትግራይና ወራቤ ብቻ ተሞክሮ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ያስቻለው “እርግብ “የትምህርት አገልግሎት የግል ድርጅት ጋር በከፍተኛ በጀት ውል ተዋውሎ በቀጣይ በሁሉም ክፍሎች ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ የመማር ማስተማር ሂደት በልዩ ስልት በመቀየስ ለመምህራን ለ20 ቀናት ስልጠና ሰጥቷል ።






