ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና ተግባራትን በመፈተሽ

ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና ተግባራትን በመፈተሽ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየሰጠ መሆኑን የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ።

ጥር 08/2018 (ወልቂጤ)

መምሪያው ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር የሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሃላፊዎች የወረዳ ፣የዞን መዋቅር የልማት ባለሙያዎች እና የህዝብ ክንፍ ተወካዮች የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ አመት የዜጎች ቻርተር የሳይንስ ፈጠራ ላይ በፓተንት እና ፕሮፖዛል አዘገጃጀት ዙርያ በልማት እቅድ ዝግጅት እና በሪፖርት አቀራረብ እንዲሁም ለህዝብ ክንፍ ስልጠና በመስጠት የባለፉት ወራት እቅድ አፈፃፀም በዛሬ ውሎ ይገመገማል ።

መክፈቻው ላይ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለጹት በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በሚሰሩ ስራዎች ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ስልጠና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን አንስተዋል ።

የተሰሩ ስራዎች በመገምገም ግብአቶችን እንደ ግብአት ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል።

ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለተገልጋዩ በቅርበት ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረገ።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረገ።

ጥር 7/2018 ዓ/ም፦(ወልቂጤ)

መምሪያው በዞኑ እስከ ቀበሌ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎታቸው እንዲያዘምኑና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲያደርጉ ለማድረግ በየዓመቱ የተሻለ ልምድ ካላቸው ተቋማት የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል!!

በዘንድሮው ዓመትም የመምሪያው ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ በዞኑ የሚገኙ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በክልላችን የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ጉብኝት በማድረግ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አካሂዷል።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ሻሜቦ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለተገኘው የዞኑ ቡድን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኃላ ስለ ማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ ገለፃ አድርገዋል!!

ዳይሬክተሩ በልምድ ልውውጡ ወቅት እንዳሉት ይህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ወሳኝ ነው!!

የጉራጌ ዞን በርካታ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በመተግበር ግንባር ቀደም መሆኑን በመግለፅ የአንድ ማዕከል አገልግሎትንም በዞኑ ተግባራዊ ቢደረግ ደግሞ ዞኑ የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባባልና ገለፃ የማዕከሉን ዳይሬክተር አመስግነው የልምድ ልውውጡ እንደዞን የጀመርነውን ዲጂታላይዜሽን አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል!!

እንደ ኃላፊው ገለፃ ምልከታው በዞኑ ያሉ ተቋማት በቴክኖሎጂ ለማዘመን ከፈተኛ ልምድ የተገኘበት ነው በማለት የዞኑ መንግስት የያዛቸውን የልማት ግቦች ለማሳለጥ አቅም የሚፈጥር እንደሆነም አመላክተዋል!!

በዲጂታል ኢትዮጲያ 2030 የተያዙ ውጥኖች እውን ለማድረግ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ማሳለጫ መንገዶች ናቸው ያሉት አቶ ደምስ በቀጣይ በዞኑም ተግባራዊ እንዲደረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በልምድ ልውውጡ የተሳተፉ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮች በጉብኝቱ መደሰታቸውን በመግለፅ ለቀጣይ የተቋም ተልእኮ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል።