



የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረገ።
መምሪያው በዞኑ እስከ ቀበሌ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎታቸው እንዲያዘምኑና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲያደርጉ ለማድረግ በየዓመቱ የተሻለ ልምድ ካላቸው ተቋማት የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል!!
በዘንድሮው ዓመትም የመምሪያው ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ በዞኑ የሚገኙ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በክልላችን የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ጉብኝት በማድረግ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አካሂዷል።
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ሻሜቦ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለተገኘው የዞኑ ቡድን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኃላ ስለ ማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ ገለፃ አድርገዋል!!
ዳይሬክተሩ በልምድ ልውውጡ ወቅት እንዳሉት ይህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ወሳኝ ነው!!
የጉራጌ ዞን በርካታ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በመተግበር ግንባር ቀደም መሆኑን በመግለፅ የአንድ ማዕከል አገልግሎትንም በዞኑ ተግባራዊ ቢደረግ ደግሞ ዞኑ የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን አመላክተዋል።
የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባባልና ገለፃ የማዕከሉን ዳይሬክተር አመስግነው የልምድ ልውውጡ እንደዞን የጀመርነውን ዲጂታላይዜሽን አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል!!
እንደ ኃላፊው ገለፃ ምልከታው በዞኑ ያሉ ተቋማት በቴክኖሎጂ ለማዘመን ከፈተኛ ልምድ የተገኘበት ነው በማለት የዞኑ መንግስት የያዛቸውን የልማት ግቦች ለማሳለጥ አቅም የሚፈጥር እንደሆነም አመላክተዋል!!
በዲጂታል ኢትዮጲያ 2030 የተያዙ ውጥኖች እውን ለማድረግ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ማሳለጫ መንገዶች ናቸው ያሉት አቶ ደምስ በቀጣይ በዞኑም ተግባራዊ እንዲደረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በልምድ ልውውጡ የተሳተፉ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮች በጉብኝቱ መደሰታቸውን በመግለፅ ለቀጣይ የተቋም ተልእኮ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል።








