ፆታ ምክንያት የሚፈጠሩ አድሉአዊ አሠራሮችንና በደሎችን እንዲወገዱ ለመታገል፣ሴቶች ማደራጀትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።

ፆታ ምክንያት የሚፈጠሩ አድሉአዊ አሠራሮችንና በደሎችን እንዲወገዱ ለመታገል፣ሴቶች ማደራጀትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።

ጥር 20/2018 ዓም (አገና )

በእዣ ወረዳ በሴቶች ማህበርና ፌዴሬሽን የሴቶች አባላት አደረጃጀትና ምሁራን በማህበር አሰራርና መመሪያ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ማደራጀትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ሰፊ ዉይይት ተካሄደ

መድረኩን ያስጀመሩት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ በአቶ አብድራህማን ሀሰን እንደገለፁት ሴቶች በተፈጠረላቸው ምቹ የፖሊሲና የህግ፣ የአሰራር፣ የአደረጃጀትና የስትራቴጂ ማዕቀፍ በመጠቀምበመረጡት ህጋዊ አላማ ዙሪያ ተደራጅተው ለላቀ ተሣትፎና ተጠቃሚነት መብቃት እንዲችሉ ትኩረት ተሰጥቶ ርብርብ መደረግ እንዳለበት ገልዋል ።

አክለውም ሴቶች በልዩ ልዩ የሴቶች አደረጃጀት ማህበራት ተደራጅተው መብቶቻቸዉንና ጥቅሞቻቸዉን በማስከበር ተሣታፊና ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ብሎም በሀገሪቱ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ስትራቴጂያዊና ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ አክለው ገልፀውልናል ።

ሰነዱ ያቀረብት የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ እንደገለፁት መደራጀት በዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች በአለም እቀፍ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት ህግጋት ዉስጥ የተፈቀደ መብትመሆኑ ገለፀው ።

በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ዜጎች የመደራጀት ያለ አንዳች ገደብ የመሣተፍ መብት አንቀፅ 31 እና በሌሎችም የሀገሪቱ ህጎች ዋስትና ተሰጥቶታል ያሉት ሀላፊው ናቸው ።

አክለውም እንዲሁም የሴቶች እኩልነት መብት አንቀፅ 35 ላይ ተደንግጎ ተቀምጧል ስለዚህም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 ላይ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸዉ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱ የሕግ አካል ሆኖ እያገለገሉ መሆኑ አሰረድተዋል ።

ከዚህም የተነሳ ሴቶች በማህበር በመሆን የግልና የጋራ መብታቸውን ለማስከበር እና የጋራ ግዴታቸውን ለመወጣት፣ የጋራ ጥቅም ለማግኘት ወይም ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ፣የሀገር ሰላምና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ዓላማ ሊደራጁ እንደሚገባ የገለፁት ሰነድ ባቀረቡበት ግዜ ነው ።

ኃላፊዋ አክለውም በማህበራዊ ህይወታቸው እንዲሁም በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ አቅማቸው ጭምር እንዲደረጁና ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ጠንካራ ሴቶችን ለመፍጠር የሴት አደራጃጀቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተሳታፊ ሴቶችም በበኩላቸው የሰላም ጉዳይ ከሁሉም ይልቅ እኛን ያሳስበናል ሰላም ከሌለ ልጅ ወልዶ መሳም የለም ሰላም ከሌለ ልማት አይኖርም ከዚህ በኋላ በሰላም ጉዳይ ላይ ወገባችንን ታጥቀን እንሰራለን በማለት ለራሳቸው ቃል ገብተዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ ምንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።

የጉራጌ ማህበረሰብ የቴሌቭዥን ጣቢያ የስቱዲዮ ግንባታ የውል ስምምነት ተፈረመ።

የጉራጌ ማህበረሰብ የቴሌቭዥን ጣቢያ የስቱዲዮ ግንባታ የውል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የፈረሙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማና የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፋስሀ በላይነህ ናቸው።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ከዛሬ አምስት አመት ጀምሮ ጉራጊኛ የሚዲያ ቋንቋ የማድረግ ስራ የጀመረው(OBN) የማህበረሰቡ የመልካም አስተዳደር እሴቶቹን እንዲለሙ ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት ዛሬ ላይ ማህበረሰቡ የራሱ የቴሌቭዥን ጣቢያ እንዲኖረው መነሳሳትን ፈጥሯል ብለዋል።

ኦቢኤን የአብሮነትና የመደመር እሴቶችን

አስፍቶ አኩሪ ባህሉን ለአለሙ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ እስካሁን በሰራቸውና ለወደፊት በሚሰራቸው ስራዎች በመላው ጉራጌ ስም አመስግነዋል።

የOBN ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍስሀ በላይነህ OBN ከዚህም በፊት የጉራጌ ማህበረሰብ የራሴ ማህበረሰብ ነው ብሎ ያደረገውን ድጋፍ አሁንም የራሱ የቴሌቭዥን ጣቢያ እንዲኖረው በሚሰራው ስራ ላይ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ተሞክሮዎችን ልምድ በማካፈል በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

በደሳወርቅ ያቦነህ

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የመንግስት ፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ቅንጅትና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ለማቋቋም የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የመንግስት ፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ቅንጅትና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ለማቋቋም የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ጥር 20/2018 ዓም

በመድረኩ የተገኙት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድራህማን ሀሰን እንዳሉት የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ትብብርና ቅንጅታቸው ማጠናከር ይገባል።

ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማምጣት የሲቭል ማህበራትና ድርጅቶች ወሳኝ አላቸው ያሉት አቶ አብድራህማን በመሆኑም በቀጣይ ሀገራዊ ተልእኮዎች በብቃት ለመፈጸም እገዛቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው በሰላም፣በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ይበልጥ እንዲሰሩ ገልፀዋል ።

የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተካ ወርቁ በበኩላቸው ይህ ምክር ቤት መቋቋም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የሚገጥማቸው ችግሮች በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የጎላ በመሆኑን እነዚህ ማህበራትና ድርጅቶች በተቋቋመው ምክር ቤት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ሳይደረግባቸው በራሳቸው ቅንጅት ፡ትብብርና አቅም እንደሚንቀሳቀሱ ባቀረቡት ሰነድ አመላክተዋል ።

በቀጣይ እነዚህ ማህበራትና ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ኃላፊነት፣ተጠያቂነትና ግልጸኝነት በመፍጠር እየሰሩት ያለ ስራ በሚመለከተው አካል እያስገመገሙ እንዲሄዱ አቶ ተካ አስገንዘበዋል።

የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እንዳለ በበኩላቸው የሲቪል ማህበራቶችና ድርጅቶች በራሳቸው በጎ ፍቃድ አምነው የገቡበት ተግባር ከምንም ነገር ነጻ ገለልተኛ በመሆን ስራቸው በአግባቡ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ።

ፍቃድ ከወስዱ በኋላ በተፈቀደላቸው ሙያ መስራት ፡እቅድና ሪፖርታቸው ማስገምገም ፡ውላቸው ማደስና ወጥ የሆነ አሰራር ተከትለው እንዲሰሩም የጠቆሙት አቶ አሸናፊ የሚገጥማቸው ችግሮችም ሆነ ቅሬታዎች ሲኖሩ ከመንግስት ተቋማት ጋር ተግባቦት ፈጥሮ ጥራት ባለው ሁኔታ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

በውይይቱ የተገኙት አካላት በበኩላቸው የጋራ ምክር ቤቱ መቋቋሙ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት በጋራ መስራት ፡የእርስ በርስ ግንኙነት መፍጠር ላይ ድርሻው የጎላ በመሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል ።

በመጨረሻም ለተቋቋመው ምክር ቤት 7 የስራ አስፈጻሚ አካላት በመምረጥ መድረኩ ተጠናቋል።