




ፆታ ምክንያት የሚፈጠሩ አድሉአዊ አሠራሮችንና በደሎችን እንዲወገዱ ለመታገል፣ሴቶች ማደራጀትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።
ጥር 20/2018 ዓም (አገና )
በእዣ ወረዳ በሴቶች ማህበርና ፌዴሬሽን የሴቶች አባላት አደረጃጀትና ምሁራን በማህበር አሰራርና መመሪያ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ማደራጀትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ሰፊ ዉይይት ተካሄደ
መድረኩን ያስጀመሩት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ በአቶ አብድራህማን ሀሰን እንደገለፁት ሴቶች በተፈጠረላቸው ምቹ የፖሊሲና የህግ፣ የአሰራር፣ የአደረጃጀትና የስትራቴጂ ማዕቀፍ በመጠቀምበመረጡት ህጋዊ አላማ ዙሪያ ተደራጅተው ለላቀ ተሣትፎና ተጠቃሚነት መብቃት እንዲችሉ ትኩረት ተሰጥቶ ርብርብ መደረግ እንዳለበት ገልዋል ።
አክለውም ሴቶች በልዩ ልዩ የሴቶች አደረጃጀት ማህበራት ተደራጅተው መብቶቻቸዉንና ጥቅሞቻቸዉን በማስከበር ተሣታፊና ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ብሎም በሀገሪቱ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ስትራቴጂያዊና ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ አክለው ገልፀውልናል ።
ሰነዱ ያቀረብት የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ እንደገለፁት መደራጀት በዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች በአለም እቀፍ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት ህግጋት ዉስጥ የተፈቀደ መብትመሆኑ ገለፀው ።
በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ዜጎች የመደራጀት ያለ አንዳች ገደብ የመሣተፍ መብት አንቀፅ 31 እና በሌሎችም የሀገሪቱ ህጎች ዋስትና ተሰጥቶታል ያሉት ሀላፊው ናቸው ።
አክለውም እንዲሁም የሴቶች እኩልነት መብት አንቀፅ 35 ላይ ተደንግጎ ተቀምጧል ስለዚህም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 ላይ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸዉ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱ የሕግ አካል ሆኖ እያገለገሉ መሆኑ አሰረድተዋል ።
ከዚህም የተነሳ ሴቶች በማህበር በመሆን የግልና የጋራ መብታቸውን ለማስከበር እና የጋራ ግዴታቸውን ለመወጣት፣ የጋራ ጥቅም ለማግኘት ወይም ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ፣የሀገር ሰላምና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ዓላማ ሊደራጁ እንደሚገባ የገለፁት ሰነድ ባቀረቡበት ግዜ ነው ።
ኃላፊዋ አክለውም በማህበራዊ ህይወታቸው እንዲሁም በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ አቅማቸው ጭምር እንዲደረጁና ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ጠንካራ ሴቶችን ለመፍጠር የሴት አደራጃጀቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ተሳታፊ ሴቶችም በበኩላቸው የሰላም ጉዳይ ከሁሉም ይልቅ እኛን ያሳስበናል ሰላም ከሌለ ልጅ ወልዶ መሳም የለም ሰላም ከሌለ ልማት አይኖርም ከዚህ በኋላ በሰላም ጉዳይ ላይ ወገባችንን ታጥቀን እንሰራለን በማለት ለራሳቸው ቃል ገብተዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ ምንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።






