


በጉራጌ ዞን የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለ10ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸው 1መቶ 86 ሰልጣኞች በአገና ከተማ እያስመረቀ ይገኛል።
የካቲት 1/2018 ዓ.ም(አገና)
ኮሌጁ በ4 የትምህርት ዘርፍ በደረጃ 2እና 4 የሚያስመርቅ ሲሆን በደረጃ 5 ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
በዚህም የምረቃ ፕሮግራም ወንድ 68 ሴት 118 በድምሩ 1መቶ 86 ያሰለጠናቸው ሰልጣኞች እየተመረቁ ነው።
ተመራቂዎችም በስልጠናው ወቅት የቀሰሙት እውቀት በመጠቀም ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ቴክኖሌጂዎችን በመፍጠርና በማላመድ የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
በምረቃ ፕሮግራሙም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ፣ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ፣ የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ፣ የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ፣ የክልል፣ የዞንና የከተማው አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ሌሎችም ተገኝተዋል።



























