የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ቅርስ የአንድ ህዝብ ማንነት፣የባህልና የሀገር እድገት መገለጫ መሆኑን በዋናነት ይጠቀሳል።

====የኢፌድሪ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ስለ ጉራጌና ክትፎ እንዲህ ብለዋል፦

ቅርስ የአንድ ህዝብ ማንነት፣የባህልና የሀገር እድገት መገለጫ መሆኑን በዋናነት ይጠቀሳል።

ጉራጌ በኢትዮጵያ እምቅ ባህላዊ ፣ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ተፈጥሮአዊ እሴቶች ባለቤት አንዱ ነው።

የጉራጌ ህዝብ ስራ የህልውና ብቻ ሳይሆን የክብር መገለጫም ጭምር ነው።

ስራን በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር ሰርቶ ያሳየ ፣ከራሱ አልፎ ለሌሎችም አራያ የሆነ ኩሩ ህዝብ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሰላም ወዳድ ከሁሉም በፍቅር የሚኖር በመሆኑ “በሰላም ገብቶ በሰላም መውጣት”ለጉራጌ ህዝብ ትልቅ ጸሎቱና ስኬቱ ነው።

ጉራጌ የብዙ ማንነቶች ምልክት ሲሆን ክትፎ የጉራጌ ማህበረሰብ መገለጫው ነው።

የጉራጌ ህዝብ ከጥልቅ የስራ ወዳድነቱ ፣ባህል ጠባቂነቱና ከጥበባዊነቱ የተነሳ የጉራጌ ክትፎ አዘገጃጀትና አመጋገብ ለመላው ኢትዮጵያዊን ወንድሞችና ለአለም ህዝብ አበርክቷል።

“ለዚህም ጉራጌዎች ኢትዮጵያ ሀገራችን ታመሰግናቸዋለች!!

የጉራጌ ክትፎ ለምግብነት ብቻ ሳይሆን የትውልድ ቅብብሎሽ፣የፍቅር መገለጫ እና የበረከት ማሳያ ነው።

ክትፎ የሌለበት ብፌ አይደምቅም ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ “ክትፎ የምግቦች አውራ ነው” ብለውታል።

ክትፎ ሲነሳ ቆጮ፣እደ ጥበብ፣ቅመሙና የአስተሳሰብ ልህቀት ተያይዘው የሚነሱ ናቸው።

ክትፎ ከጉራጌ ህዝብ አልፎ እንደ ሀገር በትልልቅ መድረኮችና አውዶች ላይ ዋና ባህላዊ ምግብ ሆኖ የሚጠቀስ በመሆኑ ባህላዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ነው።

ጥልቅ የምግብ ሙያ ይንጸባረቅበታል ፣ ባህላዊ የመመገቢያ ቁሳቁሶች በጥንቃቄ ወጥተው ጥቅም ላይ ይውሉበታል።

የአብሮነት ፣ የፍቅር፣ የመቻቻል፣የመከባበር የመተባበር እሴት ይገለጽበታ የጉራጌ ክትፎ!!

ቅርስ ማስመዝገብ የሀገር መልካም ገጽታ ለመገንባት ፣በህዝቦች መካከል የባህል ትስስር መፍጠር፣በህዝቡ ወንድማማችነትና አብሮነት እንዲጎለብት ያደርጋል።

ቅርሱ የቱሪስት መስህብነት ከፍ በማድረግ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የጉራጌ ክትፎ በአለም የትምህርት ፣የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO)ለማስመዝገብ ባለስልጣኑ በትኩረት ይሰራል እንደሚሳካም እርግጠኞች ነን።