እዣ ወረዳ የምግብና ስርዓተ ምግብ ምክር ቤት በሰቆጣ ዲክላሬሽን ዙሪያ ከክልሉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ከመጡ ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

እዣ ወረዳ የምግብና ስርዓተ ምግብ ምክር ቤት በሰቆጣ ዲክላሬሽን ዙሪያ ከክልሉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ከመጡ ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

​መጋቢት 2/2018 ዓ.ም (አገና)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ምክር ቤት፣ ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ከመጡ አካላት ጋር በሰቆጣ ዲክላሬሽን ዕቅድ ዝግጅትና በሴክተር መሥሪያ ቤቶች ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሄደ።

​በውይይቱ ላይ የተገኙት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት የምግብ ስርዓትና ስርአተ ምግብ አማካሪ አቶ ገመቹ ቁፋ እንደገለጹት፤ የሰቆጣ ዲክላሬሽን ዋነኛ ዓላማ የሆነውን “የሕፃናት መቀንጨርን እስከ 2030 (እ.ኤ.አ) ወደ ዜሮ ማውረድ” ዕውን ለማድረግ የወረዳዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም የተቀናጀ የሥርዓተ ምግብ ዕቅድ ማዘጋጀትና የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ማድረግ ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

​የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው፣ መርሃ ግብሩን ውጤታማ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ወረዳው ለፕሮግራሙ መሳካት ካለው ቁርጠኝነት መነሻ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ለፕሮግራሙ ማቺንግ ፈንድ ማስፀደቁን አስታውቀዋል።

የሰቆጣ ዲክላሬሽን ስምምነትን መሠረት ያደረገ፣ በየሴክተሩ የተከፋፈለና ግልጽ ግብ የተቀመጠለት ዕቅድ መሠረት የሚከናወን መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ችግሩ በጤና ዘርፍ ጥረት ብቻ የማይፈታ በመሆኑ፤ የግብርና፣ የውሃ፣ የትምህርትና የሴቶችና ሕፃናት ዘርፎች ያላቸውን ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

​የመረጃ ልውውጥን በማቀላጠፍና ሪፖርቶችን በትክክል በማጠናቀር ረገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የሕፃናትን ጤናና የአመጋገብ ሥርዓት ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።

​ በመድረኩ በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

የብልጽግና ፓርቲ በ2018 ጠቅላላ ምርጫ እዣ ቁ 1 የምርጫ ክልል እጩ ተወዳዳሪዎች ይፋ አደረገ

የብልጽግና ፓርቲ በ2018 ጠቅላላ ምርጫ እዣ ቁ 1 የምርጫ ክልል እጩ ተወዳዳሪዎች ይፋ አደረገ

​መጋቢት 1/2018 ዓ.ም (አገና)

የብልጽግና ፓርቲ በ2018 ዓ.ም በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በእዣ ቁ 1 ምርጫ ክልል ፓርቲውን ወክለው ለፓርላማ እና ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎቹን በይፋ አስተዋውቋል።

​ፓርቲው እጩዎቹን የመረጠው በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ልምድ እና የፓርቲውን ራዕይ ለማስፈጸም ያላቸውን ቁርጠኝነት መሰረት በማድረግ መሆኑን ገልጿል።

“ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” የሚል መሪ ቃል እና “የስንዴ ነዶን” የመወዳደሪያ ምልክት አድርጎ ወደምርጫ መግባቱን የገለፀው ፓርቲው የሀገር ጥቅምን ባስቀደመ መልኩ የሰላምና አንድነት፣ የልማት ፣ የሁለቱ ውሃዎች ፣ የዲሞክራሲ ግንባታ ጉዳዮች የምርጫ ቅስቀሳ የትኩረት ነጥቦች እንደሚሆኑም ተመልክቷል።

​በዕጩዎች ይፋ መደረግ መርሃ-ግብር ላይ እንደተገለጸው፣ ፓርቲው በምርጫው አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሚያስችለውን የምርጫ ማኒፌስቶ እና ስትራቴጂ ቀርጾ ወደ ስራ መግባቱን አመልክቷል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋን ጨምሮ የእዣ ወረዳ እና የአገና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪና ጠቅላላ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በተቋቋመው የህብረት ስራ ማህበር በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸው የ “ሶጃት” የእዣ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ህብረት ስራ ማህበር አባላት ተናገሩ ።

በተቋቋመው የህብረት ስራ ማህበር በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸው የ “ሶጃት” የእዣ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ህብረት ስራ ማህበር አባላት ተናገሩ ።

መጋቢት 1/2018 ዓም

ማህበሩ ተመስርቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበትበ አጭር ጊዜያቶች ውስጥ ጥሩ የሆነ እንቅስቃሴ እያሳየ መሆኑንም ተጠቁሟል።

አንዳንድ አስተያየታቸው የሰጡን የማህበሩ አባላት ማህበርሩ መቋቋሙ ለመንግስት ሰራተኛው ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን በመገንዘብ ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት በጉባኤ መመስሩቱን ጠቁመዋል ።

ባቋቋሙት የህብረት ስራ ማህበር በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸው ጨምረው የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ በተለይም የፍጆታ እቃዎች ከሌላ ቦታ ቅናሽ ባለው ሁኔታና በተረጋጋ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ይህ ማህበር በዚህ ልክ ወደ ስራ እንዲገባ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት እና የወረዳው መንግስት ትልቅ እገዛ ማድረጉን የሚመሰገን ነው ያሉት ተጠቃሚዎቹ ማህበሩ ትልቅና አቅም እንዲፈጥር እና ሞዴል በመሆን ለሌሎች ተሞክሮም ጭምር እንዲሆን የድርሻቸው እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ሙሉጌታ ህብረት ስራ ማህበራት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ እንደ ወረዳው በቦዠባር ከተማ ነዋሪዎች ያቋቋሙት ማህበር እና የ”ሶጃት” የእዣ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ማህበር የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ትልቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በተለይም በአገና ከተማ የሚገኘው “ሶጃት” የመንግሰት ስራተኞች ማህበርም ማህበሩ የጠነከረ እንዲሆን የከተማ መስተዳደሩ እና የወረዳው መንግስት ከመጀመሪያው አንስቶ በተለያየ መልኩ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

ማህበሩ ከመቋቋሙ አስቀድሞ እንደ ወረዳው መንግስት አስፈላጊውን ውይይት ተደርጎና መግባባት ላይ ተደርሶ በጉባኤ መመስረቱን ጨምረው የገለፁት አቶ ይድነቃቸው በአሁን ሰዓትም 11 ኮሚቴዎችና 526 አባላትም እንዳሉት ጠቁመዋል ።

ማህበሩ ሲመሰረት ከእያንዳንዱ አባላት 1200 ብር እንዲሁም 500 ሺህ ብር የወረዳው መንግስት ድጋፍ በማድረግ በድምሩ 1.2ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል በመያዝና ስራ በመጀመር ለአባላቱ ከሌላ ቦታ ከ10% – 15% ቅናሽ የተለያዩ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ማህበሩ የመንግሰት ሰራተኞች በዋጋ ንረት ምክንያት የሚደርስባቸው ኢኮኖሚያዊ ጫና በመቋቋም የኑሮ ደረጃቸው ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ያሉት ሀላፊው በቀጣይም የማህበሩ አቅም በማሳደግ ለሌሎች መሰረታዊ ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ምሳሌ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።