የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በተቋቋመው የህብረት ስራ ማህበር በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸው የ “ሶጃት” የእዣ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ህብረት ስራ ማህበር አባላት ተናገሩ ።

በተቋቋመው የህብረት ስራ ማህበር በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸው የ “ሶጃት” የእዣ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ህብረት ስራ ማህበር አባላት ተናገሩ ።

መጋቢት 1/2018 ዓም

ማህበሩ ተመስርቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበትበ አጭር ጊዜያቶች ውስጥ ጥሩ የሆነ እንቅስቃሴ እያሳየ መሆኑንም ተጠቁሟል።

አንዳንድ አስተያየታቸው የሰጡን የማህበሩ አባላት ማህበርሩ መቋቋሙ ለመንግስት ሰራተኛው ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን በመገንዘብ ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት በጉባኤ መመስሩቱን ጠቁመዋል ።

ባቋቋሙት የህብረት ስራ ማህበር በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸው ጨምረው የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ በተለይም የፍጆታ እቃዎች ከሌላ ቦታ ቅናሽ ባለው ሁኔታና በተረጋጋ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ይህ ማህበር በዚህ ልክ ወደ ስራ እንዲገባ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት እና የወረዳው መንግስት ትልቅ እገዛ ማድረጉን የሚመሰገን ነው ያሉት ተጠቃሚዎቹ ማህበሩ ትልቅና አቅም እንዲፈጥር እና ሞዴል በመሆን ለሌሎች ተሞክሮም ጭምር እንዲሆን የድርሻቸው እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ሙሉጌታ ህብረት ስራ ማህበራት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ እንደ ወረዳው በቦዠባር ከተማ ነዋሪዎች ያቋቋሙት ማህበር እና የ”ሶጃት” የእዣ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ማህበር የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ትልቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በተለይም በአገና ከተማ የሚገኘው “ሶጃት” የመንግሰት ስራተኞች ማህበርም ማህበሩ የጠነከረ እንዲሆን የከተማ መስተዳደሩ እና የወረዳው መንግስት ከመጀመሪያው አንስቶ በተለያየ መልኩ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

ማህበሩ ከመቋቋሙ አስቀድሞ እንደ ወረዳው መንግስት አስፈላጊውን ውይይት ተደርጎና መግባባት ላይ ተደርሶ በጉባኤ መመስረቱን ጨምረው የገለፁት አቶ ይድነቃቸው በአሁን ሰዓትም 11 ኮሚቴዎችና 526 አባላትም እንዳሉት ጠቁመዋል ።

ማህበሩ ሲመሰረት ከእያንዳንዱ አባላት 1200 ብር እንዲሁም 500 ሺህ ብር የወረዳው መንግስት ድጋፍ በማድረግ በድምሩ 1.2ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል በመያዝና ስራ በመጀመር ለአባላቱ ከሌላ ቦታ ከ10% – 15% ቅናሽ የተለያዩ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ማህበሩ የመንግሰት ሰራተኞች በዋጋ ንረት ምክንያት የሚደርስባቸው ኢኮኖሚያዊ ጫና በመቋቋም የኑሮ ደረጃቸው ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ያሉት ሀላፊው በቀጣይም የማህበሩ አቅም በማሳደግ ለሌሎች መሰረታዊ ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ምሳሌ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።