የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክልሉ የ1ኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን ተሸለመ።

ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

========================================================================

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት “ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ከተማ ባካሄደው የ2018 ዓ.ም የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ መድረክ፣ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክልሉ ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በላቀ አፈፃፀሙ የ1ኛ ደረጃ እውቅናና የሞተር ሽልማት ተበርክቶለታል።

ይህ አበረታች ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በዞኑ አመራር፣ በፓርቲው አባላትና በሰፊው የጉራጌ ህዝብ የተቀናጀ ጥረት፣ ጠንካራ ህዝባዊ አደረጃጀትና የጋራ ስራ ውጤት በመሆኑ ነው።

ፅህፈት ቤቱ ላስመዘገበው ውጤት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናውን እያቀረበ፤ በቀጣይም የፓርቲውን እሳቤዎች በመተግበር፣ የህዝባችንን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

ለተመዘገበው ታላቅ ውጤት በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

“ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ!

የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና

የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 81.1 በመቶው 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ተሸጋግረዋል-ምክትል ርዕሠ መስተዳድር አንተነህ ፈቃዱ

ሀምሌ 21/2018 ዓ.ም (አገና)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት አስመልክቶ መግለጫ እየሰጡ ነው።

ምክትል ርዕሠ መስተዳድሩ በመግለጫው በክልሉ በ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 88 ሺህ 927 ተማሪዎች መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

ከወሰዱት ውስጥ 81.1 በመቶው 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገራቸውን ተናግረዋል።

ይህም በ2017 ዓ.ም ከነበረው የ75 በመቶ የማለፍ ምጣኔ ጋር ሲነፃፀር የ8% እድገት ያሳየ ነው ብለዋል።

የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ በመደበኛ 50% እና በላይ፣ ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ 45% እና በላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Ⓒ የክልሉ ትምህርት ቢሮ

See less

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት

በእዣ ወረዳ ዋድዬ ቀበሌ ከዋድዬ ሚካኤል – አዲሱ ገበያ ወደ ሙህር አክሊል ወረዳ ሚያገናኘውን በመንግስት እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመንገድ ግንባታ መጠናቀቁን ተገለፀ ።

ሀምሌ 20/2018 ዓም

መንገድ ከሁሉም መሰረተ ልማቶች መካከል ዋንኛው መሆኑን በመገንዘብ በወረዳው የመንገድ ልማት ተደራሽነት ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ።

ሀምሌ 20/2018 ዓም

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ መልስ እንደገለፁት መንገድ ከሁሉም መሰረተ ልማቶች መካከል ዋንኛው መሆኑን በመገንዘብ በወረዳው የመንገድ ልማት ተደራሽ ለማድረግ በልዩ ትኩረት መሰራቱን ገልፀዋል።

እንደ ወረዳው ከዋና መንገድ እስከ ቀበሌ ማዕከል በሁሉም ቀበሌዎች ተደራሽ ከማድረግ በተጨማሪ ቀበሌ ከቀበሌ እንዲሁም መንደሮች ከቀበሌ የማስተሳሰሩ ተግባር ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መሳራቱንም ሀላፊው አመላክተዋል።

በወረዳው ዋድዬ ቀበሌ ዋድዬ ሚካኤል – አዲሱ ገበያ ወደ ሙህር አክሊል ወረዳ ሚያገናኘው የ3 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ስራ ግንባታ ጥራት ባለው መልኩ መሰራቱን የገለፁት አቶ ገዛኸኝ ይህም የመንግስት እና የማህበረሰቡ ከፍተኛ ርብርብ የታየበት ሲሆን ለረጅም ጊዜ የማህበረሰቡ ጥያቄ የፈታ በመሆኑም በዚህ ስራ የተሰማሩት አካላትም አመስግነዋል።

መንገዱ ሲሰራ የግብዓትና የማሽነሪ ድጋፍ በማድረግ የክልሉ ገጠር መንገድ ጉብሬ ዲስትሪክት ምስጋና ይገባዋል ያሉት አቶ ገዛኸኝ ከዚህ በተጨማሪ የአካባቢው ባለሀብቶች ፡ ጠንካራ ኮሚቴዎች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋልም ብለዋል ።

መንገዱ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ያሉት አቶ ገዛኸኝ በአጠቃላይ መንገዱ ደረጃው በጠበቀ መልኩ እንዲገነባ ከላይ የተጠቀሱት ባለድርሻ አካላት ጨምሮ የወረዳው መንግስት ፡ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ማኔጅመንትና ባለሙያዎች ብሎም ለመላው ማህበረሰቡ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

የፅ/ቤቱ ምክትል ሀላፊና የዩራፕ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሸምሱ ዘይኑ በበኩላቸው እንደ ወረዳው በበጀት አመቱ የአፈር ስራ 21.5 ኪ.ሜ ለማሰራት ታቅዶ 22.5ኪ.ሜ የእቅዱ 100% ተከናውኗል ብለዋል።

የጠጠር ስራ 30.7ኪ.ሜ ለመስራት ታቅዶ ከ36ኪ.ሜ በላይ መሰራቱን ያመላከቱት ሀላፊው በህ/ሰብ ተሳትፎና በመንግስት የተለያዩ የስትራክቸር ስራዎች 9 ለማሰራት ታቅዶ 8 ለመስራት ተችሏል ብለዋል።

የመንገድ ጥገና ስራ 8ኪ.ሜ ለመስራት ታቅዶ 13.5ኪ.ሜ መሰራቱን ዪመላከቱት ሀላፊው የሀብት አሰባሰብ በተመለከተም በህ/ሰብ ና በባለሀብትእንዲሁም በመንግስት 48ሚሊ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ88.4ሚሊ በላይ በመሰብሰብ የማህበረሰቡ የመንግድ ልማት ጥያቄ ደአጃ በደረጃ ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራም ይገኛል ብለዋል።

ያነጋገርናቸ በዋድዬ ቀበሌ የመንገድ ልማቱ ተጠቃሚ የሆኑት የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየትም ከዚህ በፊት መንገድ ባለመኖሩ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ጫና መፍጠሩን ጠቁመው ይህንን ችግራቸው እንዲቀረፍ ጥረት እያደረጉ ፡ መንግስት ፡ ባለሀብቶች ፡ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም መላው የአካባቢው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

See less