







በእዣ ወረዳ ዋድዬ ቀበሌ ከዋድዬ ሚካኤል – አዲሱ ገበያ ወደ ሙህር አክሊል ወረዳ ሚያገናኘውን በመንግስት እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመንገድ ግንባታ መጠናቀቁን ተገለፀ ።
ሀምሌ 20/2018 ዓም
መንገድ ከሁሉም መሰረተ ልማቶች መካከል ዋንኛው መሆኑን በመገንዘብ በወረዳው የመንገድ ልማት ተደራሽነት ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ።
ሀምሌ 20/2018 ዓም
የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ መልስ እንደገለፁት መንገድ ከሁሉም መሰረተ ልማቶች መካከል ዋንኛው መሆኑን በመገንዘብ በወረዳው የመንገድ ልማት ተደራሽ ለማድረግ በልዩ ትኩረት መሰራቱን ገልፀዋል።
እንደ ወረዳው ከዋና መንገድ እስከ ቀበሌ ማዕከል በሁሉም ቀበሌዎች ተደራሽ ከማድረግ በተጨማሪ ቀበሌ ከቀበሌ እንዲሁም መንደሮች ከቀበሌ የማስተሳሰሩ ተግባር ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መሳራቱንም ሀላፊው አመላክተዋል።
በወረዳው ዋድዬ ቀበሌ ዋድዬ ሚካኤል – አዲሱ ገበያ ወደ ሙህር አክሊል ወረዳ ሚያገናኘው የ3 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ስራ ግንባታ ጥራት ባለው መልኩ መሰራቱን የገለፁት አቶ ገዛኸኝ ይህም የመንግስት እና የማህበረሰቡ ከፍተኛ ርብርብ የታየበት ሲሆን ለረጅም ጊዜ የማህበረሰቡ ጥያቄ የፈታ በመሆኑም በዚህ ስራ የተሰማሩት አካላትም አመስግነዋል።
መንገዱ ሲሰራ የግብዓትና የማሽነሪ ድጋፍ በማድረግ የክልሉ ገጠር መንገድ ጉብሬ ዲስትሪክት ምስጋና ይገባዋል ያሉት አቶ ገዛኸኝ ከዚህ በተጨማሪ የአካባቢው ባለሀብቶች ፡ ጠንካራ ኮሚቴዎች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋልም ብለዋል ።
መንገዱ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ያሉት አቶ ገዛኸኝ በአጠቃላይ መንገዱ ደረጃው በጠበቀ መልኩ እንዲገነባ ከላይ የተጠቀሱት ባለድርሻ አካላት ጨምሮ የወረዳው መንግስት ፡ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ማኔጅመንትና ባለሙያዎች ብሎም ለመላው ማህበረሰቡ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።
የፅ/ቤቱ ምክትል ሀላፊና የዩራፕ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሸምሱ ዘይኑ በበኩላቸው እንደ ወረዳው በበጀት አመቱ የአፈር ስራ 21.5 ኪ.ሜ ለማሰራት ታቅዶ 22.5ኪ.ሜ የእቅዱ 100% ተከናውኗል ብለዋል።
የጠጠር ስራ 30.7ኪ.ሜ ለመስራት ታቅዶ ከ36ኪ.ሜ በላይ መሰራቱን ያመላከቱት ሀላፊው በህ/ሰብ ተሳትፎና በመንግስት የተለያዩ የስትራክቸር ስራዎች 9 ለማሰራት ታቅዶ 8 ለመስራት ተችሏል ብለዋል።
የመንገድ ጥገና ስራ 8ኪ.ሜ ለመስራት ታቅዶ 13.5ኪ.ሜ መሰራቱን ዪመላከቱት ሀላፊው የሀብት አሰባሰብ በተመለከተም በህ/ሰብ ና በባለሀብትእንዲሁም በመንግስት 48ሚሊ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ88.4ሚሊ በላይ በመሰብሰብ የማህበረሰቡ የመንግድ ልማት ጥያቄ ደአጃ በደረጃ ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራም ይገኛል ብለዋል።
ያነጋገርናቸ በዋድዬ ቀበሌ የመንገድ ልማቱ ተጠቃሚ የሆኑት የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየትም ከዚህ በፊት መንገድ ባለመኖሩ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ጫና መፍጠሩን ጠቁመው ይህንን ችግራቸው እንዲቀረፍ ጥረት እያደረጉ ፡ መንግስት ፡ ባለሀብቶች ፡ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም መላው የአካባቢው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
See less






