“ሰላማችን በማፅናት ለልማታችን ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን!!”

“ሰላማችን በማፅናት ለልማታችን ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን!!”

በሚል መሪቃል የ2018 ማጠቃለያ አፈፃፀም እና የ2019 ዓም እቅድ ላይ ያተኮረ ወረዳዊ የፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል ።

መስከረም 25/2019 ዓም

በመድረኩም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ፡ የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ ፡ የእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ከበደ ፡ የወረዳው አመራር ፡ ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።

See less

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በ2018 ዓም በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመገቡና ወደ አማርድ አካዳሚ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ሽኝት ተደረገላቸው ።

=========በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በ2018 ዓም በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመገቡና ወደ አማርድ አካዳሚ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ሽኝት ተደረገላቸው ።

መስከረም 23/2019 ዓም

በሽኙቱ ፕሮግራሙ የተገኙት የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንዳሉት እንደ ዞኑ ብሎም እንደ ወረዳው ብቁ ፡ ተወዳዳሪና በራሱ የሚተማመን ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲያፈራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

አማርድ አካዳሚ ከቴክኖሎጂ ጋር ፈጥነው የሚላመዱ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች የሚፈሩበት ትክክለኛ የልህቀት ማዕከል በመሆኑ ጊዜቸው በአግባቡ እንዲጠቀሙና ውጤታማ እንዲሆኑም ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዛሬው እለትም በ8 ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በአካዳሚው የመግቢያ ፈተና በመፈተን ያለፉት 10 ተማሪዎች ሽኝት መደረጉን የገለፁት አቶ ተጠምቀ ለተማሪዎችም መልካም የትምህርት ወቅት እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።

በዚህ ፕሮግራም ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ድጋፉም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሀላፊው ገልፀዋል።

ወደ አካዳሚው ከገቡ በኋላም ከዚህ ቀደም ካዳበሩት የአጠናን ዘዴ በተለይም በመደጋገፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸውም አቶ ተጠምቀ ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

See less

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ

መስከረም 23፣ 2019 (አገና)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ7ኛ ዙር መስራች ጉባዔው ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የክልሉ አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፡-

1 .አቶ ተመስገን ካሳ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

2 .ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

3 .አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ የዉሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

4 . አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የጤና ቢሮ ኃላፊ

5 . አቶ ሙስጠፋ ኢሳ የክልሉ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

6 . አቶ ሰላሙ አማዶ የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ

7 . አቶ ሳሙኤል መንገሻ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

8 . አቶ ተመስገን ጎዴቦ የክልሉ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ቢሮ ኃላፊ

9 . አቶ አሰፋ ደቼ የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ

10 .አቶ አብዶ አህመድ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

11 . አቶ አብዱል ባሲጥ አባኮ የክልሉ ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ

12 ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ

13 . አቶደምስ ገብሬ የክልሉ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ

14 ደ/ር ቶፊቅ አጫሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

15. አቶ ገብሬ ጋጌ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

16. አቶ አክሊሉ መኔዶ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ

17 . ዶ/ር ተስፈዬ አጋፋሪ የክልሉ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና የዲያስፖራ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

18 . ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

19 . አቶ ታመነ ገብሬ የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

የካቢኔ አባላቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ በመፈፀም ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል።

#ኢትዮጵያ#ትልቅሀገር#ትልቅሕዝብ#ታላቅርዕይ

See less