





=========በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በ2018 ዓም በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመገቡና ወደ አማርድ አካዳሚ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ሽኝት ተደረገላቸው ።
መስከረም 23/2019 ዓም
በሽኙቱ ፕሮግራሙ የተገኙት የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንዳሉት እንደ ዞኑ ብሎም እንደ ወረዳው ብቁ ፡ ተወዳዳሪና በራሱ የሚተማመን ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲያፈራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
አማርድ አካዳሚ ከቴክኖሎጂ ጋር ፈጥነው የሚላመዱ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች የሚፈሩበት ትክክለኛ የልህቀት ማዕከል በመሆኑ ጊዜቸው በአግባቡ እንዲጠቀሙና ውጤታማ እንዲሆኑም ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዛሬው እለትም በ8 ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በአካዳሚው የመግቢያ ፈተና በመፈተን ያለፉት 10 ተማሪዎች ሽኝት መደረጉን የገለፁት አቶ ተጠምቀ ለተማሪዎችም መልካም የትምህርት ወቅት እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።
በዚህ ፕሮግራም ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ድጋፉም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሀላፊው ገልፀዋል።
ወደ አካዳሚው ከገቡ በኋላም ከዚህ ቀደም ካዳበሩት የአጠናን ዘዴ በተለይም በመደጋገፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸውም አቶ ተጠምቀ ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
See less







