


የአገና የመጀመሪ ደረጃ ሆስፒታል የእርጉዝ እናቶች ማረፊያ በማዘጋጀት በሆስፒታሉ እንክብካቤ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ ።
እንደ ወረዳው እናቶች በተለይም በእርግዝናቸው ወቅት ተከታታይነት ያለው ክትትል እንዲያደርጉ የማስገንዘብ ስራዎች በሁሉም ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሉ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ ነው።
የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እናቶች ሊወልዱ 15 ቀን ሲቀራቸዉ በሆስፒታሉ መጥተዉ እንዲቀመጡ ማደረገ መጀመሩንም የሆስፒታሉ ስራስኪያጅ አቶ ጥላሁን ሀይሌ ገልፀዋል ።
ስራስኪያጁ አክለውም እናቶች በጤና ተቋማት በሰለጠነ ባለሙያ እንዲወልዱ በማድረግ የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ ይገባል ።
እናቶች ወደ ሆስፒታሉ ማቆያ ሲመጡ ሳይቸገሩ እና ቤታቸው ሳያስቡ በባለሙያዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው በመገንዘብ መውለጃቸው ጊዜ ሲቀራረቡ በመምጣት በሰላም እንዲገላገሉ በየቀበሌው የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ማህበረሰቡ የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም አቶ ጥላሁን መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ዘግቧል ።






