




በሀገራችን ሌብነትና ሙስና ለመከላከል የተጀመረው እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለበት የድርሻው ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ ።
በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ የ2017 ዓም ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከብሯል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ሙስናና ብልሹ አሰራር ልማትን በማዳከም የሀገር ኢኮኖሚ እንዲገታ ፡ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ፡ ህዝብ በመንግስትና በህግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ ወንጀል ነው ።
ደረጃው የተለያየ ቢሆንም በየአካባቢው ብልሹ አሰራሮች እና የሙስና ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው ሁሉም ባለበት የስራ መስክና ሀላፊነት በተለይም ሌብነት ሊኖርባቸው የሚችሉ ጉዳዮችና አካባቢዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ከራሱ በመጀመር ፀረ እድገት የሆነውን ሙስናን ለማጥፋት አስፈላጊውን ርብርብ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል ።
እንደ ወረዳው በዚህ ረገድ በሚታይ መልኩ የገነገኑ ብልሹ አሰራሮች ባይኖም በቀጣይ ሀገራችን ወደ ኋላ እየወሰዱ ካሉ ችግሮች አንዱ የሆነው ሙስና በመገንዘብ ህገ-ወጥ ተግባራት በተደራጀ መንገድ ለመከላከል ተሳትፎ ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ጥምረት ቡድን መሪ አቶ ይብሮ ሁሴን ባቀረቡት የውይይ ሰነድ ላይ እንደገለፁት በሀገራችን ሙስናን ለማጥፋት የመንግስት ቁርጠኝነት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቁመው ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀምና ተቋማዊ አሰራር በማጠናከር በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የተደራጀ ትግል ሊያደርጉ እንደሚገባም ገልፀዋል ።
የመንግስት ሀብትና ንብረት በሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይባክን ሲቪል ሰርቫንቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በመታገልና በሀገሪቱ ብሎም በወረዳው ልማትና እድገት ላይ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ ይብሮ እንደ ወረዳው ብልሹ አሰራርና ሙስናን ለመታገል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቀጣይ ርብርብ ይደረጋልም ብለዋል ።
ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየት እንደ ወረዳው በተያየ መልኩ የሚፈፀሙ ብልሹ አሰራሮች አስቀድሞ በመከላከል ስር እንዳይሰዱ ማድረግ ስለሚቻል በተለይም በየተቋሙ የተመደቡ የስነ -ምግባር ሙያተኞች በታማኝነት እና የተሰጣቸው ሀላፊነት ሙስናና ብልሹ አሰራሮች መታገልና የሚፈፅሙ አካላትም ሲኖሩ መታገል ይገባቸዋልም ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።







