የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ስራ ሂደት ላይ በመገኘት ሰራተኞችን አበረታቱ

============ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ስራ ሂደት ላይ በመገኘት ሰራተኞችን አበረታቱ

*********

በባህርዳር ከተማ የታቀደው የ22.5 ኪ.ሜ የኮሪደር ልማት የመጀመሪያ ዙር የሆነው ከገጠር-መንገድ አሮጌው ድልድይ የ3 ኪ.ሜ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ እና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኮሪደር ልማቱን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተከናወነ ያለውን የምሽት ስራ በስፍራው በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ ሰራተኞቹን አበረታትተዋል።

የኮሪደር ልማቱ በክልሉ ባህር ዳርን ጨምሮ በስምንት ዋና ዋና ከተሞች እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ስራው የከተሞችን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ዜፎች የስራ ዕድል መፍጠሩን አንስተዋል።

የኮሪደር ልማቱ የስራ ባህልን እየቀየረው፣ በምሽት መስራት እየተለመደ መምጣቱን ገልጸው፤ ይህ እውን እንዲሆን አመራሩ እና ሰራተኛው ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የከተማና መሰረት ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በክልሉ ከ47 ኪ.ሜ በላይ የኮሪደር ልማት ስራ ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በራሔል ፍሬው

#Ethiopia#ኮሪደር#ሌማት#Bhardar