የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ተማሪዎች አዋጪ በሆኑ የስልጠና መስኮች በመሰልጠን ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው የአገና ፖሊ -ቴክኒክ ኮሌጅ ጥሪ አቀረበ።

=========ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ተማሪዎች አዋጪ በሆኑ የስልጠና መስኮች በመሰልጠን ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው የአገና ፖሊ -ቴክኒክ ኮሌጅ ጥሪ አቀረበ።

ህዳር25/2017 ዓም

ኮሌጁ ለወረዳና ቀበሌ አመራር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቅበላ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጣ ስልጠኔና ሰጥቷል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ትምህርትና ስልጠና ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፡ ማህበራዊና ፖሊቲካዊ ዕድገት ቁልፍ መሳሪያ ነው ።

በዕውቀትና በክህሎት ያደገ ማህበረሰብ ቴክኖሎጂ የመፍጠርና የመጠቀም አቅሙ ያድጋል ያሉት አቶ ዘውዱ ህግና ስርዓት በማክበር እንዲሁም አካባቢውን በውል ተገንዝቦ ጥቅም ላይ ማዋል የመቻል አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በወረዳው ያለውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስገንዘብ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ በሁሉም የወረዳው ቀበሌ የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ስልጠና እንዲገቡ የቀበሌ አመራሮች በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቁና በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት ከዚህ የደረሱት የሰው ሀይል አቅማቸውን በትምህርትና ስልጠና በመገንባታቸው እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ያጠናቀቁ ወጣቶች ወደ ቴክኒክና ሙያ በማስገባት በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት ይገባልም አቶ ተሾመ አስገንዝበዋል።

የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ እለቱን አስመልክተው ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር አልያም ለመፍጠር ክህሎትና ዕውቀት አቀናጅቶ ስራ ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ እሙን በመሆኑ ለዚህ ዋነኛ መንገዱ ደግሞ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መሆኑን አመላክተዋል።

በኮሌጁ በርካታ ሰልጣኞች ሰልጥነው ውጤታማ መሆናቸው የጠቆሙት ዲኑ በአይሲቲ ዘርፍ ፡ በሆቴል ቱሪዝም ፡ በሜካኒክስ ብረታ ብረትና ፈርኒቸር ፡ በአውቶሞቲቭ ፡ በኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ ዘርፍና በአካውንቲግና ፋይናንስ ዘርፍ በመሰማራት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ እድል የፈጠሩ ወጣቶች መጥቀስ ይቻላልም ብለዋል።

ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ወደ አምራች ኢንደስትሪነት እንደሚቀየር በመገንዘብ በየቦታው 10ና 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች መጥተው በተለያየ የሙያ መስኮች የሚሰጡትን ስልጠና መርጠው በመሰልጠን ነገ ስራ ፈጣሪ እንዲሆን መላው የቀበሌ አመራር ለወጣቶቹ የማስገዘብ ስራ መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።