የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤትና የወረዳው ፍትህ ፅ/ቤት በጋራ በአገልግሎት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።

========የፍትህ ተቋማት የአገልግሎት ስርዓቱ በማሻሻል ማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ ።

ህዳር 27/2016 ዓም

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤትና የወረዳው ፍትህ ፅ/ቤት በጋራ በአገልግሎት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።

የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ሙባሪክ ግርማ እንደገለፁት የወረዳው ፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ፡ ተደራሽነትና ጥራት በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ገልፀዋል።

የዳኝነት አገልግሎት የሚያረጋግጥ ስራዎች በማከናወን ፡ የዳኝነት ነፃነት ተጠያቂነትና ገለልተኝነት ማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የዳኞችና ባለሙያዎች የመወሰን አቅም ለማሳደግ ተጨማሪ የትምህርት እድሎች የመስጠት ፡ የዳኝነት ስራው የተንዛዛ እንዳይሆን የዲጂታል ዳኝነት ከአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት ግብዓቶች የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል ።

የፍትህ ተደራሽነት በማስፋት ማህበረሰቡ ከስራው ገበታ ሳይለይ ተዘዋዋሪ ችሎት እየተሰጠበት ያለው መንገድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ህግና አሰራር በመጠበቅ መሰራቱ ለዋናው የህግ ስርአቱ አጋዥ በመሆኑ የማደራጀትና የማጠናከር ስራ ይሰራል ያሉት አቶ ሙከረም በቀጣይም አዳዲስ ህጎችና ደንቦች በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ ማህበረሰቡ መብቱና ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ በቅንጅ የመስራቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እንዳለ በበኩላቸው በተቋማቱ መልካም አስተዳደር በማስፈን በህገ-መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር እንደሚገባ በመገንዘብ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የ3 ዓመት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማዘጋጀት ከ2016 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

ከወረዳው ፍርድ ቤት ጋር በመቀናጀት ነፃ የህግ አገልግሎት ድጋፍ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ሴቶች ፡ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን እየተሰጠበት ያለው መንገድ ግንዛቤው እንዲኖር በማድረግ በተጠናከረ መንገድ መስራት ይገባል ያሉት ሀላፊው በፍትህ ዘርፍ በተለይም በፖሊስ ተቋማት አካባቢ የሚነሱ የአመለካከት ፡ የክህሎትና ፡ የስነ-ምግባር ችግሮች ለመቅረፍ በተለያየ መልኩ ስልጠናዎችና የግንዛቤ ስራዎች በመስጠት እንዲታረሙ መስራት ይጠበቃልም ብለዋል ።

የወንጀል ምርመራ ላይ ማህበረሰቡ በማሳተፍ በቅንጅት በመስራት ወንጀል የመከላከል ስራው ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ አሸናፊ የንቃተ ህግ ግንዛቤዎችና ነፃ የህግ ድጋፎችን በመስጠት በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ በተቀናጀ መንገድ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹም በሰጡት አስተያየትም እንደ ወረዳው በዘርፉ እየተሰጡ የሚገኙ ተዘዋዋሪ ችሎቶችና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚበረታቱና ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀው ከፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ጋር አልፎ አልፎ ነፃና ገለልተኛ ብሎም ከብልሹ አሰራር ጋር የሚታዩ ክፍተቶች በማረም ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ሙባሪክ ግርማ ፡ የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እንዳለና የእዣ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዳኛቸው አትርፍ የዳኝነትና የፍትህ አካላት ጥምረት ማጠናከሪያ ሰነድ ተፈራርመዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።