የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር ያቀዳቸው እቅዶችን ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ አሳሰቡ።

የካቲት 17/2017 ዓ.ም

====================

ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር ያቀዳቸው እቅዶችን ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ አሳሰቡ።

ይህ የገለጹት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ላይ ነው።

የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት ብሄራዊ ገዢ ትርክት በመገንባት ያሉ ልዩነቶችን ለሀገራዊ አንድነትና ግንባታ መጠቀም ይገባል።

የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ከመገንባት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅም ለመገንባት የተጀማመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ መስራት ይገባል ነው ያሉት።

የህዝቦችን ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተው ጠንካራ የጸጥታ አካላት ለመገንባትና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

እንደ ሀገር ዘላቂ የስራ ዕድል መፍጠር ይገባል ያሉት ሚኒስትሯ 9 ነጥብ 125 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱንም አንስተዋል።

እንደ ሀገር የኑሮ ውድነት የሚያረጋጉ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ያነሱት ክብርት ወይዘሮ ጫልቱ ለዚህም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በግብርናው ዘርፍ ከህልውና ወደ ልዕልና ለመሸጋገር ወጣቱ፣ ባለሀብቱና ሌሎችንም በማስተባበር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

መንግስት የቱሪዝም ዘርፉ ለማሳደግ ትላልቅ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን አንስተው በቀጣይም ያሉ ሀብቶችን በተገቢው በመጠቀም በዘርፉ ውጤታማ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

ዲጂታል ኢኮኖሚ መገንባት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ሚናው የላቀ በመሆኑ በዘርፉ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የከተሞች እድገት ለማፋጠን እንደ ሀገር የኮሪደር ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተው ይህም በከተማው በፍጥነት ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አውስተዋል።

የኢንዱስትሪ ምርቶችንና የመስኖ አቅም ማሳደግ እንዲሁም የትውልድ እሴት ግንባታ ማጠናከር ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ከዚህም ባለፈ የፍትህ ዘርፉ ውጤታማነት ማረጋገጥ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

እንደ ሀገር ያሉ ፈተናዎችን በጽናት በማለፍ በሁሉም መስኮችን የበለጠ ውጤታማ ስራ ከመስራት ባለፈ ፓርቲው እንደ ሀገር ያቀዳቸው እቅዶችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል። ዘገባው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።