የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ለቅድመ አንደኛ ደረጃ አመቻች መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።

የቅድመ አንደኛ ህፃናትን የሚቀርፁና የሚያስተምሩ መምህራን በሁሉም ደረጃ የተለየ ትኩረት በመስጠት ማብቃትና መደገፍ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ገለፀ።

ታህሳስ 25/2018 ዓም

ፅ/ቤቱ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ አመቻች መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።

የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንዳሉት የቅድመ አንደኛ ትምህርት በህፃናት ላይ መሰረት የሚጣልበት እና ህፃናት የተለየ እንክብካቤና ትኩረት የሚፈልጉበት ወቅት በመሆኑ ህፃናቱ የሚያስተምሩ መምህራን በዚህ ወቅት የተጣለባቸው ሀላፊት ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የቅድመ አንደኛ ህፃናት የሚቀርፁና የሚያስተምሩ መምህራን በሁሉም ደረጃ የተለየ ትኩረት በመስጠት ማብቃትና መደገፍ እንደሚገባ ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል ።

ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማራቸው የአካባቢያቸውን ባህላዊ ዕሴቶች እንዲያውቁ ፡ ቋንቋቸውን እንዲያሳድጉ ፡ ትምህርታቸውን በቀላሉ እንዲረዱና በጥሩ ስነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑን የጉራጊኛ ቋንቋ ላይ ማስተማሩን ማጠናከር እእንደሚገባም አቶ ተጠምቀ ጨምረው ተናግረዋል።

ሰልጣኝ መምህን በሰጡት አስተያየትም ህፃናት በመጀመሪያ የልጅነት ዘመናቸው የሚቀስሙት እውቀትና ክህሎት የወደፊት ስብዕናቸው የሚገነባላቸው በመሆኑ የጀመሩትን ትውልድ የመገንባት ተግባር በተቻላቸው አቅም ለማጠናከር የድርሻቸው እንደሚወጡም ተናግረዋል ።