
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ከክልሉ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

የክልሉ ህዝብ ለልማት ስራ ከ13 ቢሊየን በላይ ብር አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።
በክልሉ በትምህርት፣በጤና በመንገድ ልማት እና በሌሎችም መስኮች የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ ናቸው።
በክልሉ ሁሉም ተቋማት በእቅድ መመራት በመቻላቸው አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ነው ።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው።
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የስራ ተነሳሽነት እየጨመረ ነው።
ክልሉ ቀደም ብሎ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ወደ ተግባር በመገባቱ በቢሊየን የሚቆጠር ሀብት ማዳን ተችሏል።
በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ውጤት በፕላን እየተመራ ሲሄድ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ እንድናውቅ ይረዳናል።
የክልሉን የመልማት አቅም እንዲሁም የመረጃ ክፍተትን መለየትና መሙላት አስፈላጊ ነው።
በግብርናው መስክ የምርታማት አቅም ማመላከት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት ይገባል ።
በከተማ እና በገጠር የህዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል ።
ያለንን እምቅ አቅም በመጠቀም እቅዶቻችን ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል።
የህዝቡን የልማት ተነሳሽነት ለማጎልበት በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሀን ተከታታይነት ያለው የመረጃ ተደራሽነት ማስፋት ይገባል።
የህዝቦቸን አንድነት በሚያጠናክር የጋራ ትርክት ላይ ተመስርቶ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ማከናወን ተገቢ ነው።
የህዝብ አስተያየቶችን በግብአትነት በመውሰድ እና በማደራጀት የዘገባ ስራ ማጠናከር ተገቢ ነው።
በምርመራ፣በክስና በዳኝነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ላይ ማተኮር ፣
የመንግስት እና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ በትኩረት መስራት ይገባል ።
በአሰሪ እና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ተገቢ ነው ።
የስራ እድል ፈጠራ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ሊሰራ ይገባል።
የፋይናንስ አስተዳደር እና ሀብትን በቁጠባ ለመጠቀም የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ።
የፋይናንስ ድጋፍን ለታለመለት አገልግሎት እንዲውል በጥብቅ ዲሲፕሊን ሊመራ ይገባል።
ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ላይ የተጀመረው የድጋፍና ክትትል ስራ ውጤታማ ነው።
በክልሉ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል እና የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ከፋይናንስ ተቋማት ጋር የብድር ስምምነት መድረስተችሏል።







