










በ2017/18 ዓም በክረምት እና በበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 58 አዳዲስ ቤቶች ግንባታና 54 ቤት የመጠገን ስራዎች መሰራታቸውን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አስታወቀ ።
መጋቢት 5/2018
በዚህ በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደ ወረዳው በአጠቃላይ በ17 የስራ መስኮች 59.5 ሚሊየን ብር ሀብት አስተዋፅኦ መደረጉንም ተጠቁሟል።
የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግብረሀይል ሰብሳቢ አቶ ተሾመ ስራኒ እንዳሉት የጉራጌ ማህበረሰብ ከቀድሞ ጀምሮ የመዳዳት እሴትና ባህል አዳብሮ የመጣ ሲሆን በወአዳው የሚገኙ ወጣቶችም በዚህ ረገድ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሰማራት በርካታ ተግባራቶች ማከናወናቸውና እያከናወኑ ይገኛሉ ።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች እውቀታቸው ጊዜአቸውና ገንዘባቸውን በተለያየ መልኩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖችን አስተዋፅኦ የሚያደርጉበት ነው ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው በዚህ ዘርፍ በየቀበሌው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመለየትና ከወጣቱ ጋር መግባባት በመፍጠር በተከናወኑት ስራ ስራ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውም ገልፀዋል።
ይህ ተግባር ውጤታማ እንዲሆን እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራቶች በየጊዜው በመገምገምና ጠንካራ ስራዎች ይበልጥ በማጠናከር ጉለቶች ሲኖሩ በፍጥነት እንዲታረሙ በማድረግ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተሾመ በሂደቱም ሰው ተኮር የሆኑ ተጨባጭ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ጠንካራ ስራዎች መሰራታቸውንና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ ነሪ እንደገለፁት በወረዳው የሚገኙ ወጣቶች በየቀበሌአቸው በማህበርና ፌዴሬሽን አደረጃጀቶችን በማጠናከርና የወጣቱ የስብዕና ግንባታ ስራዎች በመስራት ወጣቱ ሰራ ፈጣሪ ሆነው እራሳቸው ችለው ተጠቃሚ ከመሆናቸውም ባሻገር በክረምት እና በጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡ በተለያዩ አገልግሎቶች እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም ወጣቱ ከሱስና ካልባሌ ቦታዎች እንዲርቅ በቂ ግንዛቤ ተፈጥሮለት በየአካባቢው የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች አዳዲስ ቤት በመገንባትና በመጠገን ፡ እርሻ በማረስና በሌሎችም አርዕያነት ያላቸው ተግባራቶች ተሰማርተው ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል ።
ይህ ተግባር እንደ ወረዳው በአብይና ቴክኒክ ኮሜቴ እየተገመገመ የሚመራ ሲሆን ይህም ጠንካራና ውጤታማ ስራ ለመስራት ማስቻሉንም የተናገሩት አቶ ፍቅሬ በየቀበሌው ወጣቱ በራስ ተነሳሽነትም ጭምር እያደረገው ያለው ማህበረሰቡ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ምስጋና የሚገባው ሲሆን ይህም በላቀ ደረጃ ማስቀጠል እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የፅ/ቤቱ ምክትልና የወጣት ማብቃት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ታበዞ በበኩላቸው በወረዳው እንደ አጠቃላይ በበጋና ክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 17 የስራ መስኮች ላይ ችግርተኞችን በመለየት 58 አዲስ ቤት 54 እድሳት ስራ መከናወኑ ጠቁመው ይህም ወጣቱ ጨምሮ የወረዳው መንግስት ፡ ባለሀብትና ሌሎችም አካላት በማስተባበር የተከናወኑ መሆናቸውም ገልፀዋል።
ሌላ ከግብርና አንፃር ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች መሬታቸው 80.5 ሄክታር ከማረስ በተጨማሪ ምርጥ ዘር ብሎም ማዳበሪያ ጭምር ድጋፍ የማድረግ ስራ ማከናወን ተችሏል ያሉት ም/ ሀላፊው ከዚህ በተጨማሪ የሰብል አሰባሰብ ስራ ፡ በጤናው ዘርፍ ፡ በትምህርት ፡ በመሰረት ልማት ስራዎችና ፡ የዘማች ቤተሰብ ድጋፍና ሌሎችም ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።
በአጠቃላይ በ17 የስራ መስኮች 59.5 ሚሊየን ብር ሀብት አስተዋፅኦ መደረጉንም የገለፁት አቶ ጌታቸው ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ወጣቱ በየአካባቢው ሰለቸኝ ሳይል ለማህበረሰቡ በተለያየ መልኩ እያደረገው ያለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ያነጋገርናቸው በበጎ ፈቃድ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ ስራ መስራት ከሰብአዊነት ባሻገር ለህሊና እርካ ጭምር በመሆኑ ያለማንም አስገዳጅነት ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ጠቁመው ይም በቀጣይ በላቀ ደረጃ በማስቀጠል የማህበረሰቡ ችግር በተቻላቸው አቅም ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤት የተሰራላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችም በሰጡት አስተያየት ለዘመናት በአቅም ችግር ምክንያት ቤታቸው በመጉዳቱ እንደሚያፈስባቸውና አንዳንዶቹ ሙሉ በሙሉ በመፍረሱ ከጎረቤት ተጠግተው እየኖሩ እንደነበር አስታውሰው በአሁን ሰዓት ግን የአካባቢው ወጣቶች ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት የቤት ባለቤት በመሆናቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮግ ፅ/ቤት ነው ።






