





ከሁከት ነፃ የሆነን የግጭት አፈታት ባህል እንዲጎልበት የሚሊሻ አባላት በስነምግባር እና ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ።
መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (አገና )
በእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና በእዣ ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት በጋራ የተዘጋጀ በግጭት ቅድመ መከላከል መፍታትና በሰላም እሴት ግንባታ፤ በፀጥታ መረጃ ዙሪያ ለሚሊሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠናና የደንብ ልብስ የማልበስ ስራ ተሠርቷል።
የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ ስልጠናው በወረዳችን የተጀመሩ መልካም አስተዳደር እና የልማት ስራዎች በመስራት የሰላም እሴት መገንባት የግጭት ቅድመ መከላከል በመጠቀም መከባበር አንድነት ፍቅርና መቻቻል እንዲከበር በማድረግ ከሁከት ነፃ የሆነን የግጭት አፈታት ባህል እንዲጎልበት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
አክለውም ሚሊሻ ከስራው ሳይነጠል የአካባቢ ሰላም መጠበቅ ወንጀል እንዳይፈፀም መከታተልና መከላከል እና በአካባቢ ህግና ስርዓት የሚያስከብር ነው ወንጀል የመከላከል ስራም ሆነው ወንጀል ፈጽሞ ሲገኝ በቅርበት ተከታትሎ በማቅረብ የማይናቅ ሚና ይጫወታል በማለት አሰረድተዋል።
የእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ከበደ እንደገለፁት የሚሊሻ አባላት ዋነኛ ሚናቸው ህገወጥ ድርጊቶች በመቆጣጠርና በመከላከል የአካባቢ ሰላምና ፀጥታ ማስከበር ሲሆን ይህንን ለመፈፀምም የሚሊሻ አባላት ስነምግባር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
በተለይም ህገወጥ ንግድ/ኮንትሮባንድ/፣ የስርቆት ወንጀል፣ ህገወጥ አረቄ ስርጭት፣ የደን ጭፍጨፋ እና መሰል ድርጊት እንዳይፈፀሙና ተፈፅመው ሲገኙም ከወረዳ የፀጥታ መዋቅር አፋጣኝ መረጃ በመለዋወጥ ህግ የማስከበር ስራ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም የ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ የቀበሌ ሚሊሻ አባላት ከሰላም ወዳዱ ማህበረሰባችን በመቀናጀት ሊፈፅሙት የሚገባ ሚና የጎላ መሆን አለበት ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ሚ/ጽ/ቤት ሀለፊ አቶ ሲሳይ ክፈተው እንደገለፁት የሚሊሻ አባላት ሕግ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እና ማስከበር አካባቢያቸውን ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋ የመከላከል እና የማረጋጋት ስራዎች መስራት እንዳለባቸው ገልፀው
አስቸኳይ የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ ሁኔታዎች እንዳይባባስ አፋጣኝ እርምጃዎች መውሰድ ሁኔታውን የማረጋጋት እና በቁጥጥር ስር ለመዋል እንዲቻል በአስቸኳይ የመረጃ ማድረስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ለ145 የሚሊሻ አባላት የደንብ ልብስ የማልበስ ስራ ተሰርቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።






