ተማሪዎችና መምህራን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አቅማቸውን በማጎልበት የፈጠራ ችሎታቸውን ከፍ ማደረግ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ገለፀ ።
ህዳር 1/2019 ዓም
የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እና የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት በጋራ የተዘጋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ክትትል አቅም ግምባታ የ2018 ዓም አፈጻጸም ዙርያ ለ2019 ዓ/ም ማጠናከርያ የተዘጋጀ የንቅናቂ መድረክና የሳይንስ ሳምንት አከባበር በክበባት አደረጃጀት እና በአዕምሮዊ ንበረት ጥበቃ የተሰጠ ስልጠና።
ስልጠናው የሰጡት የጉራጌ ዞን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ክትትል አቅም ግምባታ የ2018 ዓም አፈጻጸም ዙርያ ለ2019 ዓ/ም ማማጠናከርያ መምሪያ የፈጠራ ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ አብይ ወልደ ሰንበት እንደገለፁት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባት ድጋፍና አደረጃጀት ስራዎች የሚከተሉት ላይ በዋናነት እንደሚሰራ ገልፀውልናል ።
ተማሪዎችና መምህራን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አቅማቸውን በማጎልበት የፈጠራ ችሎታቸውን ከፍ ማደረግ ፣በሳይንስና በሒሳብ ትምህርት መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር የፈጠራ ስራቸውን ለማህበረሰቡ ችግር ፈችና ምርምር የተካነበት ስራዎችን በማሳደግ ውጤታማ ማድረግእና የሳይንስና ቴክኖሎጂ የኢኖቬሽን ስራን ወደ ማህበረሰቡ እንዲስረጽ ማድረግ እንደሁም ተማሪዎችና መምህራን በሳይንስና በሒሳብ ትምህርት ከጽንሰ ሀሳብ በተጨማሪ የተግባር ስራዎች እንዲሰሩ ማድረግና ወደ ተግባር እንዲለውጡ ማድረግ እንደሆነ የገለፁት አቶ አብይ ናቸው ።
አክለውም ሳይንስ ማለት ነባራዊውን አለም እና የተፈጥሮ ህግጋትንና ክስተቶችን ለማብራራትና ለመገንዘብ የሚያስችለንን ዕውቀት በምልከታና በሙከራ የምናገኝበት ዘዴ መሆኑ ገለፀው ቴክኖሎጂ ሳይንሳዊ ዕዉቀትን ተግባራዊ በማድረግ የሚገኝ እና የተወዳዳሪነት እና የማድረግ አቅም የሚያሻሽል ማንኛዉም አሰራር፤አደረጃጀት፤ስርዓት ወይም ቁስ ማለት እንደሆነ እና ኢኖቬሽን ማለት የተፈጠረ ቴክኖሎጂን የሚያሻሽል መሆኑ አሰረድተዋል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ የትምህርት ፅ/ቤት መ/ሀላፊ አቶ አስቻለው ወልዴ እንደገለፁት ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት በህብረተሰቡ ውስጥ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት ማጥበብ እንደሚገባ ገለፀው ።
ለዚህም ትልቅ እድል ሚፈጥረው በትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ የሚቻሉባቸው በቂና ምቹ የሆነ ምህዳር መፍጠር እንደሚገባም ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።
አክለውም ለሁሉለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶችን ለማሳደግ በተለይም የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ሀላፊነት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ፡፡
የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ተወካይ እና ኢኮቴ ስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ ትዝታ ሳህሌ እንደገለፁት የፈጠራ ስራዎችን በትምህርት ቤት ደረጃ በስፋት እንዲተገበሩ መደገፍና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑ አሳስበዋል ።
በመድረኩ የተሳተፉት ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየትም ተቋሙ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመው አሁንም እስከ ትምህርት ተቋማት ድረስ በመውረድ እያከናወነው ያለው ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል ።
በእለቱም በተቋሙ በ2018 ዓም በጀት ዓም ጥሩ አፈፃፀም ያላቸው ከ1- 3 የወጡ ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።












