


የተለያዩ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ያልተፈቀዱ ለስላሳ መጠጦች ፡ ለምግብነትና ለመዋቢያነት የሚውሉ ምርቶች ሰብስቦ ማስወገዱን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ተቋሙ ከተጣለበት ሀላፊነቶች መካከል የሸማቹ ማህበረሰብ መብት ማስጠበቅ አንዱ ሲሆን በተለያዩ ወቅቶች ለህብረተሰቡ የሚሸጡ እቃዎች ደረጃቸውና የአገልግሎት ጊዜአቸው በመፈተሽ የንግድ ተቋማት ላይ በተለያየ ጊዜ ክትትል እየተደረገ ይገኛልም ።
ከዚህ በተጨማሪም እንደሀገር ቁጥጥር ይደረግባቸው የተባሉ ምርቶች ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም በተለያዩ ጊዜያቶች የግንዛቤ ስራ እየተሰራ ቢሆንም አሁንም ነጋዴዎች በማወቅም ባለማወቅ የሚሸጡ እንዳለና እነዚህም ከተጠያቂነት የማይድኑ በመሆናቸው የእርምት እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።
በዛሬው እለትም ለማህበረሰቡ ጠንቅ የሆኑ የተለያዩ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች የለስላሳ መጠጦች ፈሳሽ ቅባት ሻይ ቅጠል እና የተለያዬ የሸቀጥ ቁሳቁሶች የንግድ ባለሙያ የወረዳው ወንጀል መከላከል ፖሊስ የጤና ተወካይ በተገኙበት የማስወገድ ስራ መሰራቱንም የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ሙሉጌታ ገልፀዋል።







