




====ለዉጡን በማስቀጠልና የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በማጎልበትና በማፅናት ሂደት የፖሊስ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ “የጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ለታደሰ ቁመና”በሚል ሀሳብ ለፖሊስ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋለም ብዛ በሀገር ደረጃ መንግስት ለጸጥታና ደህንነት ተቋማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው የፖሊስ አገልግሎት ደግሞ የሰው ዘር ለሆነ ሁሉ የሚሰጥና የዜጎች የለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከየተኛውም ወንጀልና ወንጀል ነክ ጉደዮች ሰላማዊ እንዲሆን የሚሰራ ተቋም ነውም ብለዋል ።
የለውጡ መንግስትም ባለፉት ሰባት ዓመታት የፖሊስ እና የፀጥታ እንዲሁም የደህንነት ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ያሉት አቶ ይርጋለም በዚህም በፖሊስና በጸጥታ ተቋማት እንዲሁም በደህንነት ዘርፉ ላይ በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
የእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ከበደ በበኩላቸው ለዉጡን በማስቀጠልና የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በማጎልበትና በማፅናት ሂደት ደግሞ የፖሊስ ሚና ከፍተኛ መሆኑንና የፖሊስ ተቋም በየጊዜው የሚመጡ ለውጦችና እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተገቢው ተገንዝቦ እንቅፋቶችን መከላከል ይጠበቅበታል ብለዋል ።
ፖሊስ ለልማትና ለኢኮኖሚ ግንባታ መሠረት የሆነዉ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን በትጋት ከመሥራት ባሻገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ግንባታ ዓምዶች ተገንዝቦ ለኢኮኖሚ ብልፅግና መሥራት ይጠበቅበታል ያሉት ሀላፊው ማህበረሰቡ በተለያዩ መልኩ የሚያንሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማቃለል ሂደት ፖሊስ ትልቅ እገዛ ማድረግ እንደሚችል በመገንዘብ በእዣ ወረዳ የሚገኙትን የፖሊስ አባላት የድርሻቸውን መወጣት አለባቸውም ብለዋል ።
በቀጣይም አጠቃላይ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከመደበኛ ህግ ማስከበር ተግባራት ጋር በመቃኛት ማህበረሰቡን ማገልገል ይገባል ያሉት አቶ ደሳለኝ ጂኦስትራቴጂያዊ ለውጦችን አውቆ ወደ ተግባር መግባት የፖሊሳዊ ቁመናችንና ዝግጁነታችን በላቀ ደረጃ ማሳደግ ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዳኛቸው አትርፎ የስልጠናው ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱም የፖሊስ ተቋም የሀገርን ዳር ድንበር ከመጠበቅ ባሻገር የህብረተሰቡን ሠላምና ፀጥታ የማረጋገጥ ተልዕኮ ያለዉ ሲሆን ከዚህ ባሻገርም በተቋሙ የውስጥ አገልግሎት አሰጣጥም ላይ ያሉ ችግሮችን በማሻሻል ማህበረሰቡ በመንግሥት ላይ ያለው አመኔታ ከፍ እንዲል መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል ።
“ከጂኦ ስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚሰጠው ስልጠና ማህበረሰቡን ከሚያማርሩ የአገልግሎት አሰጣጥ በመላቀቅ በስነምግባር በመታነጽ ማህበረሰብን የማገልገል አስፈላጊነትን የሚጎላብት መሆን አለበት ያሉት የፖሊስ አዛዥ ዳኛቸው በሀገር ደረጃ የተሰሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ያስገኙት ጂኦ ስትራቴጂያዊ የበላይነትና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲሁም ፖለቲካዊ ድሎችና ፈተናዎችም ላይ ሆነን የምንሰራ በመሆኑ ከፍ ያለ ሀላፊነት ይዞ መስራት ይገባል ብለዋል ።
ሰልጣኝ የፖሊስ አባላት በሰጡት አስተያየትም ስልጠናው የፖሊስ አባላትን በጂኦ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤን በማሳደግ፣ የሀገርን ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ አቅማቸውን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል በመሆኑ ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በተግባር ለማዋል መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።







