የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መቆጣጠር

================================

የካቲት 21/2016 ዓም
“”””””””””””””””””””””””””'”‘ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠርና የንግድ ህግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ በማድረግ የኑሮ ውድነትን መቀነስና የህ/ሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ ።
የእዣ ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት በህገ-ወጥ የንግድና እንቅስቃሴዎች፡ በንግድ ገበያ ማዕቀፎች እና ፀረ -ኮንትሮባንድ ግብረ ሃይል ኮሚቴ አደረጃጀት ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ መስጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሸምሱ አክመል እንደገለፁት በወረዳው የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች እያመጣ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ሲሆን ወደ ህጋዊነት ስርዓት በማምጣት አጋዠ የሆኑ አካላት ግንዛቤ እንዲያገኙ በማስቻል ህጋዊ ስርዓትን በማዘመን ትክክለኛና ውጤታማ የንግድ ስርዓት በመፍጠር ይገባል።
የንግድ አሰራር ዘመናዊ ፣የተቀላጠፈና ፍትሀዊ በማድረግ የሸማቹን ፣ የንግዱን ህብረተሰብና የመንግስትን ሚዛናዊ ጥቅም በማስከበር የንግድ ዘርፍ የወረዳው የኢኮኖሚ እድገት የሚደግፍበትን ሚና ለማሳደግ የቅንጅት ተግባር አስፈላጊ መሆኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪው ጨምረው ገልፀዋል ።
በንግዱ ማህበረሰብ ፣ በሸማቹና በንግድ ተቋሙ የሚታዩ የአመለካከትና አሰራር ችግሮችን በመቅረፍ በተለይም በንግድና በግብይት ስርዓቱ ውስጥ የሚታየውን ብልሹ አሰራር በመፈተሽና ቀጣይ እንደ ወረዳው ውጤቱ የሚታይ ተግባር እንዲኖር መስራት እንደሚገባም አቶ ሸምሱ ተናግረዋል ።
የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ከበደ በበኩላቸው እንደገለፁት ሁላችንም ከቃላት በመውጣት ለህብረተሰቡ በመቆርቆር የሚጠበቅብንን እየሰራን የምንሄድ ከሆነ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።
ሀላፊው አያይዘውም የትኛውም የማህበረሰብ ክፍል ህገወጥ አሰራሮችን በመቃወም ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥሙት ወደ ህግ አካል በማቅረብ መፍትሔ እንዲሰጥ ማድረግና ህጉን ተከትለው የሚሰሩትን ደግሞ በማበረታታት አሁን እየገጠሙን ላሉ ችግሮች ተባብረን መፍትሄ የምንፈልግ መሆን አለብን ብለዋል።
በፅ/ቤቱ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሪጉሌሽን ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሺለጋ ምራኒ በህገ-ወጥ የንግድና እንቅስቃሴዎች፡ በንግድ ገበያ ማዕቀፎች ፀረ -ኮንትሮባንድ ዙሪያ ላይ ትኩረት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የንግድ ህግና ደንብ በመተላለፍ የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ ለሀገራችን ብሎም ለወረዳው ኢኮኖሚ እና ህጋዊ ለሆነው የግብይት ሥርዓት ፈተና መሆኑን በሰነዱ አመላክተዋል።
ያለንግድ ፈቃድመነገድ፣ ከተፈቀድ መጠንና ኮታ በላይ ምርትን ማዘዋወርና ማከማቸት፤ እጥረትን ለመፍጠር ምርት አከማችቶ መያዝ፤ ያለበቂ ምክንያት በምርቶች ላይ ዋጋ ጨምሮ መሸጥ፤ ምርቶችን አለግባብ መሰብሰብ፣ ማከማቸትና ማዟዟር፤ የንግድ ፍቃድን ለሶሰተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠትና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በማዳከም ለልማትና ለዕድገት የሚደረገውን ርብርብ እየተፈታተነ የሚገኙህገ-ወጥ ድርጊቶች በመሆናቸው ሁሉም በተቀናጀ መንገድ መታገል እንደሚያስፈልግም በሰነዱ አመላክተዋል።
ተሳታፊዎች ህገወጥ ንግድ ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ ቆራጥነትና ተነሳሽነተ ስለሚያስፈልግ ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል ።
በእሰቱም ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር /ፀረ-ኮንትሮባንድ / ግብረሃይል ኮሚቴ አደረጃጀት ፡ ሀላፊነት እና የቀጣይ እቅድ ቀረቦ ውይይት ተደርጎአል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።