የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ለአገና ጤና ጣቢያ የአልትራሳውንድ የህክምና መሳሪያ ድጋፍ የተደረገ በመሆኑ በቅርብ ቀን አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተቋሙ አስታውቋል ።

========ለአገና ጤና ጣቢያ የአልትራሳውንድ የህክምና መሳሪያ ድጋፍ የተደረገ በመሆኑ በቅርብ ቀን አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተቋሙ አስታውቋል ።

ይህ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል ድጋፍ የተደረገው የአልቶራሳውንዱ መሳሪያ እርጉዝ እናቶች ወደ ሌላ የህክምና ተቋም በመሄድ ይደርስባቸው የነበረው እንግልት የሚያስቀር ሲሆን የረጅም ጊዜ የተቋሙ ብሎም የማህበረሰቡ ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ተግባር መሆኑንም ተጠቁሟል።

የአገና ጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ከድር እንዳሉት ጤና ጣቢያው ገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከረጅም ጊዜ አንስቶ ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ሲያገለግል ቆይቷል ።

ጤና ጣቢያው ከሚሰጣቸው የህክምና አገልግሎት አንዱና ዋንኛው የእናቶችና ህፃናት ሞት ለመቀነስ የሚደረግ አገልግሎት ሲሆን በዚህም ረገድ እንደ ክልሉ ብሎም እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ ተግባራቶች እያከናወነ እንደሚገኝም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

በተለይም የእርጉዝ እናቶች ማረፊያ አገልግሎት በመጀመር እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ በጤና ተቋም እንዲገላገሉ በማድረጉ ረገድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ሸምሱ ለዚህም የሚያግዝ የእናቶች ማረፊያ ክፍል በመገንባት እናቶች እንደራሳቸው ቤት ምቾት እንዲሰማቸው ለማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በርካታ ተግባራት እየተሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል ።

በበጀት ዓመቱ በጤና ጣቢያው በእስካሁን ሂደት በርካታ እናቶች የቅድመ ወልዲ አገልግሎት በመስጠት ከታቀደው 108% ያህል መፈፀሙን የጠቆሙት ሀላፊው በግማሽ ዓመቱ ከታቀደው 105% እናቶች የወሊድ አገልግሎት ተሰጥቷልም ብለዋል ።

ይህ በክልሉ በክልሉ በኩል ድጋፍ የተደረገው የአልትራሳውንድ መሳሪያ ከዚህ በፊት ለጅም ጊዜ ጥያቄ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሸምሱ ይህም ከወሊድ ጋር ተያይዞ ትክክለኛ የፅንስ ሂደቶች በመከታተል ጤናማ እናትና ልጅ እንዲኖር ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልፀዋል ።

የአልትራሳውንድ አገልግሎቱ በከተማ መስተዳደሩና በወረዳው የሚገኙ 14 ቀበሌዎች ተጠቃሚ በማድረግ በዓመት ከ600 በላይ የሚሆኑ እናቶች አገልግሎት መስጠት የሚያችል መሆኑንም የገለፁት ሀላፊው እናቶች ለዚህ አገልግሎት ሲሉ ወደ ሌላ ተቋም በመሄድ ይደርስባቸው የነበረው እንግልት የሚያስቀር በመሆኑንም ይህን ድጋፍ ላደረገው የክልሉ ጤና ቢሮ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በእናቶች ማረፊያ ክፍል አግኝተን ያነጋገርናቸው እናቶች በሰጡት አስተያየት በማረፊው ክፍላቸው ከህክምናው ክትትል በተጨማሪ ልክ ቤታቸው እንዳሉ አስፈላጊውን እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀው ከዚህ በተጨማሪ ሌላ ቦታ ሳይሄዱ በአቅራቢያቸው የአልትራሳውንድ ህክምና እንዲያገኙ ለደገፋቸው አካል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።