






መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መንገድ ትኩረት ሰጥቶ እያበረታታ እና ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለፀ።
ቀን 26/05/2018
በእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበር ጉዳዮች ጽ/ቤት ከወረደው መንግስት ጋር በመቀናጀት 300,000 ብር ወጪ በማድረግ ለዘጠኝ (9) የአካል ጉዳተኞች ዌልቸርና እንዲሁም ለሌሎች ለአራት (4) አካል ጉዳተኞች የክራንች ድጋፍ አደረገ።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እዳሉት አካል ጉዳተኞችን ማገዝ ከኢትዮጵያዊነት ባህል አኳያና ከመንፈሳዊ ርካታ በተጨማሪ ለሃገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ትልቅ አስተዋፆ እዳለው በመረዳት መንግስት እና ፖርቲ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና።
በተለይም እንደ ሃገር አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር እና ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀው ።
በተቻለ መጠን ሁሉም አካል ጉዳተኞችን ማቀፍ መደገፍ ምቹ ነገሮችን መፍጠር ተገቢ እንደሆነና በየትኛውም በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አካል ጉዳተኞችን ማበረታታት እንደሚገባ እና በተለያዩ ጊዜም ይህ በጎ ተግባር ሊቀጥል እና ሊጎለብት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የእዣ ወረዳ የሰ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትግስት መንግስቴ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት እስከ 300,000 ሺ ብር ወጪ በማድረግ ለ9 አካል ጉዳተኞች ና ለተጨማሪ 4 አካል ጉዳተኞች የክራንች ድጋፍ ያደረገ መሆኑን ገልጸው።
በወረዳው ማዕከል ለተለያዩ አካል ጉዳተኞች ሲንቀሳቀሱ መጸዳጃ እንዳይቸገሩ በማሰብ የአካል ጉዳተኞች ምቹ የሚሆን ሽንት ቤት መግባቱን ገልጸው ከዚህም በተጨማሪ ሌሎችም ድጋፊችን እየተደረገላቸው እንደሆነ አስረድተው።
አሁንም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከመቼውም ጊዜ በላይ ከዘመኑ እሳቤ ጋር አብሮ የሚራመድ የሰለጠነ አስተሳሰብ እና ዘላቂ ለውጥ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ማህበረሰብን ለማሳወቅ እና የተሻለ ማህበራዊ እድገት ለማስመዝገብ እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት ሁሉም አካላት የበኩሉን ሊወጣ እደሚገባ አስገንዝበዋል።
አካል ጉዳተኞችን በበኩላቸው የወረደው መንግስት በተለያየ ጊዜ አካል ጉዳተኞች እየረዳና እያገዘ እንደሆነ ገልፀው አሁንም ከመንግስት ባገኙት ድጋፍ መደሳቸውንና በተለያየ ጊዜም ይህ ተግባር ሊቀጥል እንደሚገባና የተደረገላቸውን የድጋፍ እቃዎች በመረከብ የድጋፍ ስርዓቱ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።







