የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ አረቄ፣ናፍጣና ቤንዚን በቁጥጥር ስር ዋለ።

=====የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ የብሔራዊ መረጃ ደህንነትና የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በጋራ በመሆን በተሰራው ኦፕሬሽን በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ አረቄ፣ናፍጣና ቤንዚን በቁጥጥር ስር ዋለ።

ጥር 2/2018 ዓ.ም(አገና)

በዞኑ ህገወጥነትን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ አስታውቋል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ነጋ አስፋው እንዳሉት የማህበረሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ 1 መቶ 50 ጀሪኪና አንድ በርሜል አረቄ መምሪያው ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንደዚሁም ከወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት በጋራ በመሆን በተሰራው ኦፕሬሽን በመያዝ የማስወገድ ስራ ተሰርቷል።

ከዚህም ባለፈ 96 ጀረኪና ናፍጣና 18 በርሜል ቤንዚል በኦፖሬሽኑ ስለመያዙንም ኃላፊው ተናግረዋል።

በዞኑ ህገወጥነትን ለመከላከል መምሪያው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ይታገሱ ደሳለኝ በበኩላቸው በህገወጥ መንገድ የተያዘው አረቄ የት እንደሚመረት የማይታወቅ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበትና የህብረተሰቡን ጤና የሚጎዳ መሆኑን ጠቁመው ይህም ማታ 1 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት በተሰራው ኦፕሬሽን መያዙን ተናግረዋል።

ይህ ህገወጡ አረቄ ከዚህ ቀደም የበርካታ ህብረተሰብ ጤና መጎዳቱና ለህልፈት መዳረጉን አንስተው ህገወጥ አረቄ ለማስወገድ የተጀመረው የኦፕሬሽን ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ከዚህም ባሻገር በከተማው በህገወጥ መንገድ ቤንዚልና ናፍጣ በኦፖሬሽኑ መያዙንም ገልጸዋል።

ኃላፊው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር እያደረገ ያለው ህገወጥነትን የመከላከል ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ዘገባው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው።