
=============================
በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የአፈፃፀም አቅማቸው በማጠናከር የህዝቡን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ ።
በእዣ ወረዳ የቀበሌ ምክር ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ/ፎረም በዝግባቦቶ ቀበሌ በዛሬው እለት ተካሂዷል ።
በእለቱ የእዣ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ እንደለገለፁ የቀበሌ ምክር ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ /ፎረም/ ዋና አላማው በወረዳ ደረጃ የሚገኙ ምክር ቤቶች ካላባቸው የአፈፃፀም ጉድለት እንዲቀርፉ በማድረግ ከሌሎች ልምድ በመውሰድ ለወከላቸው ማህበረሰብ በተገቢው ለማገልገልና በቁርጠኝነት ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል ።
ዋና አፈ-ጉባኤው አክለውም በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የህዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ ዋና አላማ በማድረግ የተመሰረቱ መሆናቸዉን አስረድተዉ በቀበሌው የህዝቡ ችግሮች በመለየትና እንዲፈቱ በተቻለ አቅም ጥረት ማድረግ ፡ ጉባኤዎችን በወቅቱ በማከናወን ፡ በቀበሌው የሚከናወኑ ተግባራቶች ቁጥጥርና ክትትል በማጠናከር የህዝቡ የልማትና መልካም አስተዳደሮች እንዲፈቱ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በዛሬው እለትም በዝግባቦቶ ቀበሌ ፎረሙን የተካሄደበት ዋና ትኩረቱም አንዳንድ ችግር ያለባቸዉ ቀበሌዎችን ከሌሎች ሞዴል ቀበሌዎች የልምድ ልዉዉጥ በማድረግ በመቀመር ፣ የአካልና የመስክ ልየታ በማድረግና ሁሉም ቀበሌዎች ካለባቸው ችግር እንዲላቀቁ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለባቸውም አቶ ሙከረም ገልፀዋል ።
የእዣ ወረዳ ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሰናይት ሳህሌ በበኩላቸው በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የክትትልና ቁጥጥር አቅማቸው በማሳደግ የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ መስራት አለባቸው ብለዋል ።
የቀበሌ ምክር ቤት ተግባራት የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የተናገሩት ም/አፈ ጉባኤዋ ህዝቡን የጣለባቸዉን አደራ ለመወጣት የሚያጋጥማቸዉ ችግሮችን በመለየት በቀበሌዉ ለሚፈለጉ ልማቶች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል ።
በፎረሙም በተለያየ አፈፃፀም ደረጃ ያሉ ም/ቤቶች ሪፓርት በማቅረብ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን አንድ አንድ ቀበሌዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች የተሻሉ መሆናቸዉ፣ በሚደረጉ የድጋፍና ክትትሎች የተሻለ ለዉጥ እያስገኘ እንደሆነ ፣በጥንካሬ ጎን የተነሱ ሀሳቦች ሲሆኑ በተወሰኑ ቀበሌዎቸ የጉባኤ መቆራረጥ መኖሩ፡ በቅንጅት ከመስራት ጋር እና ሌሎችም ክፍተት በመኖሩ እነዚህ በጉድለት የተነሱ ጉዳዮች በቀጣይ መፈታት እንዳባቸው ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።
የፎረሙ ታዳሚዎች በሰጡት አስተያየትም የምክክር መድረኩን በየቀበሌ መደረጉን ከተሻሉ ቀበሌዎች ልምድ የሚቀመርበት መሆንኑ ጠቅሰው በቀጣይም በቀበሌ ምክር ቤቱ ያዩት ተሞክሮ በየቀበሌያቸው እንደሚያከናውኑም በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።






