የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለተከታታይ 25 ቀናት በተከናወነው የ2017 ዓም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተግባር 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተለያዩ ስትራክቸሮች መልማቱን ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለተከታታይ 25 ቀናት በተከናወነው የ2017 ዓም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተግባር 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተለያዩ ስትራክቸሮች መልማቱን ተገለፀ።

የ2017 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ መዝግያ ፕሮግራም በወረዳው በኮኬራ ቀበሌ ኖርቻ ንዑስ ተፋሰስ ተካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በመዝጊያው ፕሮግራም ወቅት እንደገለፁት የዘንድሮው ተፋሰስ ልማት ስራ መላው የወረዳው ህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ የተሳተፉበት መሆኑን ተከትሎ የሚታዩና ለግብርናው ዘርፍ እጅግ አጋዥ የሆኑ ስራዎችን መሰራታቸውን አመላክተዋል።

ይህ የተፋሰስ ልማት ተግባር ከሚከናወኑ ጠቃሚ ስራዎች በተጓዳኝ ህብረተሰቡ እንደየ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ሰፊ እድል የፈጠረ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ በቀጣይም መላው አርሶአደሩ ይህንኑ አደረጃጀት በመጠቀም በበልግ ልማትና በሌሎችም ተግባራቶች ጠንካራ ስራ በመስራት እንደ ሀገር የመለወጥ ግብ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በተደራጀ መልኩ የተፈጥሮ ሀብታን በመጠበቅ ፡ በማልማትና በላቀ ደረጃ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ መግባባት በመፍጠር እንዲሁም ከሌላ ጊዜያቶች በተለየ መልኩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እንቅስቃሴ መደረጉን ተከትሎ ጠንካራ ስራ ተሰርቷል።

በአጠቃላይ በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ህዝቡ ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ በተለይም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችሉ በሌላ አካባቢዎች የምንሰማቸውና እንደ እዣ ወረዳ ቢከናወኑ ተብሎ የታለሙ እንደ ጠረጴዛማ እርከን እና በሌሎችም ስራዎች እጅግ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ ተሾመ ይህ ተሞክሮ በጠንካራ አደረጃጀቶች በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ተግባራዊ ማድረግ እንሚገባም አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በዘንድሮ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር 7ሺ 880 ለማልማት የታቀደ ሲሆን 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተመረጡ 28 ነባር ንዑስ ተፋሰሶችም የየተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ከታቀደው እቅድ በላይ ለማሳካት ተችሏል ብለዋል ።

በተፋሰስ ልማቱም በልዩ ትኩረት ከተፈፀሙ የፊዚካል ስትራክቸሮች መካከል የጠረጴዛ ርከን ፡ የአፈር ካብ ፡ ትሬንች ፡ የእንጨት ክትርና ሌሎችም ስራዎች በተመረጡ ቦታዎች መሰራታቸውን የገለፁት አቶ መቻል በቀጣይም ተግባሩ ከስነ -ህይወታዊ ስራ ጋር በማሳለጥ ቀጣይነት ያለውና አስተማሪ የሆነ ስራ ይሰራልም ብለዋል ።

ይህ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር እንደ ወረዳው መዝጊያ ፕሮግራም ቢደረግም እንኳ በቀጣይ በSLM ፕሮጀት የታቀፉ ቀበሌዎች እስከ ሰኔ ወር ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።

በፕሮግራሙ የተሳፈቱ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሰጡቱ አስተያየት በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ህዝቡ ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ ባለቤ ሆኖ ያለማንም ጠባቂነት ማከናወኑን የቻለበትና እጅግ የተለየና ለግብርና ምርታማነት ማሳደግ አስተዋፅኦ ያለው የጠረጴዛማ እርከን ስራ መከናወኑ ይበል የሚያሰኝና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።

በእለቱም በ2017ዓም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር ከSLM ፕሮጀክት ጋር በመቀናጀት የተከናወኑ የጠረጴዛማ እርከንና ሌሎችም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራቶች በተሳታፊዎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በአፈፃፀም ግንባር ቀደም የሆኑ ቀበሌዎችና አደረጃጀቶች የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።